የአርሲ ኦርቶዶክሳውያን ጉዳይ ለአሜሪካ መንግሥት ቀረበ
======
( Adebabay ሚዲያ ሕዳር 30/2018 ዓ.ም):-
ባለፉት ሁለት ዓመታት በአርሲ “የተቃጠሉ ቤተሰቦችን፣ በግፍ የተገደሉ ካህናትንና ምእመናንን፣ የወደሙ አብያተ ክርስቲያናት እና ለመኖር የሚታገሉ ኦርቶዶክሳውያንን የሰነድ ማስረጃ ለአሜሪካ የዓለም አቀፍ የሃይማኖት ነጻነት ቢሮ (U.S. Office of International Religious Freedom) በሰፊው አቅርበናል፤ መፍትሔ እስኪገኝ ድረስ ተልእኳችን ይቀጥላል። አጀንዳችንን አንቀይርም!!” ሲሉ ሒደቱን ካስተባበሩት ኦርቶዶክሳውያን አንዱ የሆኑት ዲ/ን ፋሲካው ካሣው በፌስቡክ ገጻቸው አስታወቀዋል።
ትናንት ሰኞ ለአሜሪካ የሃይማኖት ነጻነት ቢሮ ጉዳዩን ካቀረቡት መካከል ብፁዕ አቡነ ሉቃስ፣ አባ ገብርኤል በቀለ (ዶ/ር)፣ መልአከ ጥበብ ቀሲስ ሳሙኤል ግዛው እንደሚገኙበት ከዲ/ን ፋሲካው መልዕክት ለመረዳት ተችሏል።
የሃይማኖት ነጻነት ቢሮ (U.S. Office of International Religious Freedom) ካሉት ተግባርና ኃላፊነቶች መካከል፦
** በመላው ዓለም ያለውን የሃይማኖት ነጻነት ጉዳይ መከታተል (Monitoring religious freedom conditions around the world)፣
** ሃይማኖትን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶችን መመዝገብና መሰነድ (Documenting violations of religious freedom—including persecution, discrimination, detention, killings, and destruction of religious sites)፣
** ዓመታዊ ሪፖርቶችን ማጠናቀርና ማቅረብ (Producing the annual U.S. International Religious Freedom Report, which evaluates every country’s performance on protecting or violating religious freedom)፣
** የአሜሪካ መንግሥትን የውጪ ፖሊሲ በተመለከተ የምክር አገልግሎት መስጠት (Advising U.S. foreign policy so that religious freedom becomes part of America’s diplomatic and human-rights work) እንዲሁም
** ሃይማኖትን መሠረት ያደረጉ መንግሥታትና ግለሰቦች ላይ ለአሜሪካ መንግሥት የማዕቀብ ርምጃዎች መነሻ ሐሳብ ማቅረብ (Recommending actions such as sanctions or designations (e.g., Countries of Particular Concern) for governments that commit severe violations) የሚሉት ይገኙባቸዋል።
የሰማዕታቱን ደም ከንቱ የማያደርግ እግዚአብሔር የተጀመረውን በጎ ተግባር ከፍጻሜ ያድርስልን።