ህዳር 26፣ 2018 (ዲሰምበር 5፣2025)
በነፃነት የመሰብሰብን መብት በማፈን የሚፀና ሥርዓት አይኖር፤ ብልጽግናም ራቁቱን ቀርቷል!
ኢህአፓ ህጋዊና መሰረታዊ መብቱን በመጠቀምና ህጋዊ መንገድን በመከተል አዲስ አበባ ላይ ለህዳር 27፣ 2018
(December6, 2025) የህዝብ ስብሰባ ለማድረግ ዝግጅቱን ሁሉ አጠናቆ እንደነበር በሰፊው ይታወቃል። የአዲስ አበባወጣትም ይህን ሰብሰባ ለማታደም በከፍተኛ ጉጉት ሲጠብቅ እንደነበር የተለያዩ መረጃዎች አሳይተዋል፡፡
ሆኖም ግን በመጨረሻው ሰዓት ላይ ብልፅግና ስብሰባው እንዳይካሄድ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ መንገድየተለመደዉን የዲሞክራሲ ሆነ የዜጎች በነፃነት የመስብሰብ መብት አፈናዉን በመጠቀም ስብሰባው እንዳይካሄድአድርጓል፡፡
በዚህ ተግባሩ ብልጽግና ፀረ ዴሞክራሲነቱን ይበልጥ አያረጋገጠ ብቻ ሳይሆን ህዝቡን ከአዳራሽ ውስጥ ስብሰባ በላይለከፋ አመፅ እንዲዘጋጅ እያደረገውም ጭምር ነው።
ብልጽግና ለህዳር 27፣ 2018 ኢህአፓ የጠራውን ህዝባዊ ስብሰባ በሰላም እንዲካሄድ ሊፈቅድ እንደማይችል ቀደምሲልም ተገማች ቢሆንም በተለይም ምርጫ ይካሄዳል በሚባልበት በአሁኑ ሰዓት መሆኑ ደግሞ በሀገራችን ወስጥነጻና የህዝብ ፍላጎት በትክክል የሚገለጥበት ምርጫ ለማካሄድ እንደማይቻል የህዝብን መሰረታዊ መብት ማክበርየአገዛዙ ፍላጎት እንዳልሆነ ይበልጥ የተረጋገጠበት ይፋ ማስረጃም ነው፡፡
ህዝብ የሚፈልገውን ለመምረጥ አማራጮቹ እነማን እንደሆኑ ማውቅ መብቱ ነው፡፡ ይህን ማድረግ ደግሞመሰብሰብንና በተቃዋሚነት የቆሙ አማራጭ አይሎች የሚያቀርቡትን ራዕይ ማወቅ የሚችልበት ምህዳር እንዲኖርግድ ይላል፡፡ ባለፉት ሰባት የአገዛዝ ዘመኑ ብልጽግና ምን እንደሆነ በግልፅ የሚታወቅ ቢሆንም በዚህ የስብሰባማደናቀፍ ተግባሩ ደግሞ እውነተኛ ገጽታውን ፀረ ዴሞክራሲና አፋኝ አገዛዝ መሆኑን ይበልጥ እንዲታይ አድርጓል፡፡ይህ ህዝባችን ሊሸከመው የማይችለውና የማይገባውም ዘግኛኝ ጉዳይ ነው፡፡
ኢሕአፓ በአዲስ አበባ እንዲካሄድ ጠርቶት የነበረው ስብሰባ ህዝቡ በዕለት ተዕለት ህይወቱ እየገጠመው በሚገኘውማቆሚያ የሌለው የከፋ የኑሮ ውድነት፤ ራሱንም ቤተሰቡንም ለማቆየት የዕለት ጉርስ፣ለመጠለያው የቤት ኪራይ
የሚሆን አጥቶ ባለበትና አጠቃላይ ኑሮውን አሣዛኝና እጅግ አስጨናቂ ባደረገው የሀገሪቱ ሁኔታ ላይ ለመመካከር ነበር፡፡
ጥሪው የህዝብ ብሶት መገለጫ የህዝብንም ብሶት ማሰተጋቢያ ነበር ፡፡
ስብሰባው ህዝብ በሰበብ አስባቡ፣ ወደ እስር የሚወረወርበት፤ በልማት ስም ዜጎች በግፍ የሚፈናቀሉበት፣በማንናታቸውና በእምነታቸው የሚሳደዱበት የሚዋከቡበት የሚገደሉበት ሁኔታ ለመነጋገር ዜጎች በሰላምወጥተውመግባት አስተማማኝ ባልሆነበት፣ በዚህ አገዛዝ ስር ንብረታችው እየተነጠቀ በልማት ስም እንደእቃ የሚወረወሩበትጉዳይ ላይ ለመወያየት ይህም የሚያበቃበትን በጋራ ለመመልከት ነበር፡፡
ስብሰባው ወጣቱ ሥራ ማግኘት ለምን አንዳልቻለ፣ በሀገሩ እንደልቡ ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሶ መሥራትም ሆነ በሰላም መኖር ለምን አንዳልቻለ፣ አንገቱን ቀና አድርጎ መሄድ ለምን እንዳልቻለ፣በሀገራችን ውስጥ የሚታየው ወገኖቻችንንእየጨረሰ የሚገኘው ጦርነት ምክንያቱ ምን እንደሆነ፣ በአጠቃላይም ወጣቱን አዛውንቱንም ሴቱንም ወንዱንምእያስጨነቀና ተስፋ እንዲያጣ እያደረገው ያለው ምን እንደሆን በጋራ እንዲመካክርና በጋራም መፍትሄ እንዲፈልግለማድረግ ነበር፡፡
ከዚህ በተፃራሪ ብልፅግና የወሰደው ዕርምጃ፣ ይህን የህዝብ ብሶት ህዝብ እንዳይነጋገርበት ማድረግ፣ ህዝብን በዚህሰቆቃ ስር በፍርሀት ተሸብቦ በስልጣን ለመቀጠል እንጂ ችግሩን ለመፍታት በፍጹም እንደማይፈቅድ ማሳያ ነው፡፡
ህዝብ ደግሞ በባርነት ሰቆቃ መኖር አይገባውም፤ አይፈልግምም፡፡
ህዝብ ይህን የራሱን ጉድይ ለመነጋገር የሚችልበት የስብሰባ አዳራሽ ግብር እየከፈለ በሚኖርበት የራሱ በሆነችውና እጅግ ብዙ አዳራሽ በሚገኝባት ከተማው በአዲስ አበባ እንድ አዳራሽ ለተወሰኑ ሰዓቶች መከልከሉ ህዝብ በአዲስ አበባ
ውስጥ የሚፈቀድለት የበይ ተመልካች ሆኖ እንዲኖር ብቻ መሆኑን ማሳያ ነው፡፡ ይህ በምንም መልኩ ተቀባይነትየለውም በትዕግስት ሊታለፍም አይገባም፡፡
ከላይ የተገለጠው የአገዛዙ ተግባር ሁሉ ሀገወጥ ብቻ ሳይሆን ከህዝብ ፍላጎት በተጻራሪ የቆመ ህዝብን ለበለጠ ተስፋመቁረጥ ፣ ለበለጠ ድህነት፣ ለበለጠ መፈናቀል ለበለጠ ብስጭት ወዘተ የሚዳርግ ሀገርንም አደጋ ላይ የሚጥል ነውና
በጥብቅ ልንቃወመውና ልንታገለው ይገባል፡፡ ገዢዎች ኢትዮጰያንም ይሁን ህዝባችንን እንደፈለጉ እንዲያደርጓቸው መፍቀድ እጅግ አስነዋሪ ብቻ ሳይሆን በታሪክም አስወቃሽ ነውና ምንም አይነት ቅቡልነት ሊኖረው አይገባም፤ አይችልምም፡፡
የህዝባችን ትግል አሁንም ሀገርን ለማጽናት ህዝቡም ሙሉ መብቱን እንዲጎናፀፍ እንጂ በግፈኞች ስር ተንበርክኮየፈለጉትን ቀንበር ጭነውበት እንዲኖር አይደልም።
ኢሕአፓ ይህ እንዲሆን በፍጹም አይፈቅድም፡፡
እንደድርጅትየሕዝባችንን ዕኩልነት ነጻነት፣ የመብት መከብር ወዘተ እስኪረጋገጥ የሀገራችንም አንድነት በማይናወጥ መሰረት ላይእስኪቆም ድረስ አስፈላጊውን መስዋእትነት እየከፈለ ትግሉን ይቀጥላላ እንጂ ሸብረክ አይልም፡፡
ለዚህም መሥረታዊዓላማ እንታገላለን የምትሉ ኢትዮጵያዉያን ሁሉ ከኢሕአፓ ጎን በመቆም በምትችሉት ሁሉ መንገድ እንድታግዙትእንጠይቃለን፡፡
ይህ የአዳራሽ ክልከላና ማደናቀፍ ትግሉን ይበልጥ እንድናጠናክር እንጂ ወደ ኋላ እንድናፈገፍግ አያደርገንም፡፡
እኛ በውጭ ሀገር የምንገኝ የኢሕአፓ ደጋፊዎችም ድርጅቱ ለህዝባችን ለወገኖቻችን ለሀገራችን ከሚያካሂደው ትግል ጎን የቆምን መሆኑን አሁንም እናረጋግጣለን፡፡
በሁሉም ቦታ የሚገኙ ለዴሞክራሲ ለአንድነት ለእኩልነት የቆሙሁሉ በኢሕአፓና በአዲስ አበባ ህዝብ ላይ የተደረገውን በቀጥታም ይሁን በተዛዋሪ በሰላም የመሰብሰብ መብትክልከላና የማደናቀፍ ተግባር እንዲያወግዙና የትግል አንድነታቸውንም በሁሉም መልክ እንዲገልጹ በአክብሮትእንጠይቃለን፡፡
የህዝባችንን መሰረታዊ መብት ለማስከበር በጽናት እንታገል፡፡
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!
የኢሕአፓ የውጭ ድጋፍ አስተብባሪ ኮሚቴ