ፋኖ የብልፅግናው ቡድን ቁልፍ የመረጃና ደህንነት አባላት የነበሩ አራት ሰላዮች ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ።
የምድር ኃይል እና የአየር ኃይል በሙሉ አቅሙ ካሰለፈው የብልፅግና አገዛዝ ጋር ገጥሞ ድል እየተቀዳጀ የሚገኘው የፋኖ ኃይል፡ አሁን ደግሞ የዚኸው ፀረ አማራ አገዛዝ ቁልፍ የመረጃና ደህንነት ሰዎች ናቸው ባላቸው ላይ ከወትሮው በተለየ ሁኔታ ጥብቅ እርምጃ እየወሰደባቸው ይገኛል።
ከቀናት በፊት የራያ ቆቦ ወረዳና የሰሜን ወሎ ዞን መረጃና ደህንነት ቡድን ቁልፍ ሰው የነበረው አቶ ጥጋቡ ደርቤ የተባለ ደህንነት ከነ አጃቢዎቹ መገደሉን መዘገቡ አይዘነጋም።
በራያ ቆቦ ወረዳና በሌሎች የዞኑ አከባቢዎች እየተንቀሳቀሱ “የፋኖ ደጋፊ ናቸው፣ ፋኖን የተቀላቀለ ቤተሰብ አላቸው፣ ብልፅግና ፓርቲን አይደግፉም፣ በየስብሰባው ከመንግስት የሚወርዱ መመሪያዎችን ይተቻሉ” በሚል ንፁኋንን በገፍ ሲያስረሽኑ፣ በጅምላ ሲያሳስሩ የነበሩ አራት ሰላዮች በፋኖ ስናይፐር ጥይት ተመተው ግብአተ መሬታየው ተፈፅሟል።
እነዚህ የመረጃና ደህንነት ቡድን አባላት ንፀኋንን በገፍ ከማስረሸንና ከማሳሰር በተጨማሪ በውጊያ ወቅት የድሮን፣ የመድፍና የሞርተር እንዲሁም የሌሎች ከባባድ መሣሪያዎች አስተኳሽ በመሆን ንፁኋንን ለእልቂት የዳረጉ፡ ታሪክ በጥቁር መዝገቡ በደማቁ ያሰፈራቸው የዘመናችን ባንዳዎች ነበሩ።
በአፋብኃ ምኒልክ ዕዝ ስር የምስራቅ አማራ ኮር 2 ቃኞች ህዳር 24/2018 ዓ/ም አመሻሹን በራያ ቆቦ ወረዳ ልዩ ቦታው አራዱም ወታደራዊ ካምፕ ዙሪያ ላይ በፈፀሙት የተጠና ጥቃት፡ ጉሽሽ ደረስ የተባለ ሕዝብ ያስለቀሰ ደህንነትን ጨምሮ አራት የመረጃና ደህንነት አባላትን መግደላቸውን በላከው መረጃ ያሳወቀው ዕዙ፡ እርምጃው ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል ገልጿል።
ቆቦ ከተማን ጨምሮ የራያ ቆቦ ወረዳ እና የሰሜን ወሎ ዞን የመረጃ እና ደህንነት አባል በመሆን ንፁኋንን “የፋኖ ደጋፊ ናቸ፡ ፋኖን የተቀላቀለ ቤተሰብ አላቸው” በሚል እያሳፈነ እንዲሁም የድሮን አስተኳሽ በማሰማራት ለአገዛዙ ሲላላክ የነበረው አቶ ጥጋቡ ደርቤ ህዳር 17/2018 ዓ/ም ማለዳ ከነ አጃቢዎቹ በተወሰደበት ጥቃት ሕይወቱ ማለፉን በወቅቱ ጣቢያችን የአይን እማኞችንና ምኒልክ ዕዝን ዋቢ አድርጎ መዘገቡ አይዘነጋም።