ኤርትራ ያገተቻቸውንየአዘርባጃን ጀልባዎችንና ዜጎችን ልትለቅ ነው

ኤርትራ፣ በኅዳር ወር ያገተቻቸውን ሦስት የአዘርባጃን አሳ አጥማጅ ጀልባዎችንና የአዘርባጃን ዜጎች የኾኑትን ሠራተኞች ለመልቀቅ ዝግጅት እያደረገች መኾኗን ባለሥልጣናቷ እንደገለጡ የአዘርባጃን የዜና ምንጮች ዘግበዋል።

የኤርትራ ባለሥልጣናት ጀልባዎቹን ለሦስት ወራት ያህል ያገቱት፣ እንዲህ ያለ ክስተት ሲያጋጥም ሰፊ ምርመራ ለማድረግ የአገሪቱ ሕግ ስለሚፈቅድ እንደኾነ መናገራቸውን ዘገባዎቹ ጠቅሰዋል።

በሦስቱ ጀልባዎች ውስጥ ታግተው የሚገኙት 18 የአዘርባጃን ዜጎች በመልካም ጤንነት ላይ ይገኛሉ ተብሏል።

ጀልባዎቹ ቀይ ባሕር ላይ የታገቱት፣ በአየር ጸባይ ለውጣ ሳቢያ አቅጣጫ ቀይረው ወደ ኤርትራ የባሕር ግዛት በገቡበት ወቅት ነበር።