የምኒልክ ዕዝ አሃዶች በጥምረት ዳውንት እና ፀሃይ መውጫ ላይ ታላቅ ድል ተጎናፀፉ::
የምኒልክ ዕዝ አሃዶች በጥምረት ዳውንት እና ፀሃይ መውጫ ላይ ዛሬ ህዳር 23/2018 ዓ.ም ማለዳ 3:00 ጀምሮ እስከ ቀን 6:00 ከፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት ጋር በመፋለም ታላቅ ድል አስመዝግበዋል::
ጠላት ዳውንት እና ፀሃይ መውጫ ከተማን ለመቆጣጠር ከኮንና ጋሼና አንድ ክፍለጦር ዙ23ን ጨምሮ እንዲሁም ከወገል ጤና አንድ ክፍለ ጦር ዙ 23 ጋር ወደ ዳውንትና ፀሃይ መውጫ ማጥቃት ያደረገ ሲሆን ከምስራቅ አማራ ኮር 2 ዞብል አምባ ክፍለ ጦር እና ከደጋው መብረቅ ኮር ከፅናት መክትና ሰንጥቅ ክፍለ ጦር የተውጣጡ ሻለቆች እንዲሁም ሌሎች በመደራጀት ላይ ያሉ አሃዶች በጥምረት የጠላትን ሰራዊት ለጊዜው በስም ያልታወቁ አመራሮችን ጨምሮ በመደምሰስና በማቁሰል ከባድ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ በማድረስ ብሎም ቀጠናውንና ከተሞቹን በማስከበር ታላቅ ድል ተጎናፅፈዋል::
በዚህ በድንቅ መናበብ በተመዘገበ ታላቅ ፍልሚያና ድል የጠላት ሰራዊት በሁሉም አቅጣጫ የተመታ ሲሆን አስከሬንና ቁስለኛውንም እያነሳ ወደመጣበት አቅጣጫ ሽሽቷል:: በተጋድሎው በመደራጀት ላይ ያለ የልዩ ዘመቻ አሃድም የተሳተፈ ሲሆን ከልጅ እያሱ ኮር 23ኛ ክፍለ ጦር አንድ ጓድ በውጊያ መሃል ደፈጣ ጥቃት በመፈፀም ታላቅ ጀብድ ሰርተዋል::
በዚህ ታላቅ ተጋድሎ ከባድ ምት የተመታው አገዛዙ ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ የገባ ሲሆን የደላንታና የወገል ጤና የብልፅግና ካድሬዎችና አመራሮች ተከበናል መላም የለን እያሉ ወደ ደሴ ከተማ መሸሽ ጀምረዋል:: ውጊያው አሁንም ሌሎች አሃዶች ተጨምረውበት ተጠናክሮ ቀጥሏል::
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ