አስደማሚው የጎንደሩ ተጋድሎ እና የተገኘው ድል!
በማዕከላዊ ጎንደር ቡርኳስን፣ ዳዋ ዳሞትና ምንዝሮ ላይ በተደረገ ውጊያ 12 የአገዛዙ ወታደሮች ሲገደሉ ከ17 በላይ የሚሆኑት መቁሰላቸው ተሰምቷል!
በአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ ዳግማዊ ቴዎድሮስ ኮር ስር የሚገኘው ግዙፉ የጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር ትናንት ህዳር 22/2018 ዓ/ም በጠላት ላይ ከባድ እርምጃ በመውሰድ ታላቅ ድል መቀዳጀቱን ከክፍለጦሩ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ለማረጋገጥ ችሏል።
ከማዕከላዊ ጎንደር ጠዳ፣ ከማክሰኝት እና ከደጎማ ከተሞች ተሰባስቦ በዞኑ ስር ዳዋ ዳሞት፣ ምንዝሮ እና ቡርቧክስ በተባሉ አከባቢ ላይ በከባድ መሣሪያ ታግዞ ጥቃት ከፍቶ የነበረው የፀረ አማራው አገዛዝ ኃይል፡ ከወደ ፋኖ የተከፈተበትን የፀረ ማጥቃት መቋቋም አቅቶት ሙትና ቁስለኛውን ማንሳት እስኪያቅጠው ድረስ መፈርጠጡ ታውቋል።
ትናንት ከንጋት ጀምሮ እስከ ቀኑ 9:00 ሰዓት በተደረገው አውደ ውጊያው በጎንደሬ በጋሻው ክፍለጦር ስር ፋሲለደስ ፣ቃኘው እና ጎንደር ብርጌድ የተሳተፉ ሲሆን በኦፕሬሽኑ ከ12 በላይ ጠላት ሲገደል፡ ከ17 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ክፋኛ ቆስለዋል።