ካርቱም የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች የሱዳን ጦር ሠራዊት “የበቀል ጥቃት” እንዳሰጋቸው ገለፁ

ካርቱም የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች፣ ከተማዋን መልሶ ለመቆጣጠር የተቃረበው የሱዳን ጦር ሠራዊት “የበቀል ጥቃት” ይፈጽምብናል የሚል ስጋት እንዳደረባቸው ሪፖርተር ዘግቧል።

በከተማዋ የሚኖሩ 70 የሚጠጉ ኢትዮጵያዊያን ስጋት ያደረባቸው፣ የሱዳን ፈጥኖ ደራሹ ኃይል ከአንድ ዓመት ከስድስት ወር በፊት ከተማዋን ሲቆጣጠር እዚያው በመቆየታቸው እንደኾነ መናገራቸውን ዘገባው ጠቅሷል።

ኢትዮጵያዊያኑ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ጣልቃ ገብቶ እንዲረዳቸው ተማጽኖ ማቅረባቸውንም ዘገባው ጠቅሷል።

ጦር ሠራዊቱ በቅርቡ የአልጀዚራ ግዛትን መልሶ ሲቆጣጠር፣ በግዛቲቷ የሚኖሩ በርካታ ደቡብ ሱዳናዊያን ለፈጥኖ ደራሹ ኃይል ድጋፍ አድርገዋል በሚል ጥርጣሬ በበቀል ስሜት እንደተገደሉ አይዘነጋም።