የአብይ አሕመድ ድሮን ተመትቶ ወደቀ!

በትላንትናው ዕለት ማለትም ሕዳር 1 ቀን 2018 ዓ.ም በአፋር በረሀሌ ላይ ጥቃት ለመፈፀም እንደሔደ በተፈፀመበት ጥቃት ተመትቶ እንደወደቀ የኢትዮ 251 ሚዲያ ምንጮች ከአፋር ገልፀዋል።

ምንጮች አክለውም ባለፉት ቀናት አካባቢው ላይ ከፍተኛ የድሮን አሰሳና ጥቃት ጭምር እንደነበር የገለፁ ሲሆን በትላንትናው ዕለት ግን ድሮኑ ተመትቶ እንደወደቀ ገልፀዋል።

“ድሮኑ ተመትቶ ከወደቀ በኋላ ለአሰሳም ይሁን ለጥቃት ተጨማሪ ድሮን በሰማይ ላይ አላየንም።” ሲሉ የአካባቢው ምንጮች ለ251 ሚዲያ ገልፀዋል።

አብይ አሕመድ 11 ድሮኖችን እንደታጠቀና ከትላንቱ ጥቃት በኋላ 10 እንደቀሩት የታወቀ ሲሆን፤ ባለፉት ወራት ብቻ ከ60 እስከ 70 የሚደርሱ የድሮን ጥቃቶችን እንዳደረገ የታወቀ ሲሆን የራሱን ዜጎች ለማጥቃት ከፍተኛ የሀገሪቱን ሀብት እያባከነ እንደሆነ ተገልጿል።

በአየር ኃይልና በቤተመንግስት ከፍተኛ ትርምስ እንደተፈጠረ ለማወቅ ችለናል።

ኢትዮ 251 ሚዲያ