ሕወሃት፣ ፌደራል መንግሥቱ በትግራይ ላይ የድሮን ጥቃት ፈጽሟል ሲል ከሠሠ

የድሮን ጥቃቱ በትግራይ ጸጥታ ኃይሎች እና በነዋሪዎች ላይ ጉዳት አድርሷል ያለው ሕወሃት፣ ፌደራል መንግሥቱ በዚህ ጥቃት የፕሪቶሪያውን የግጭት ማቆም ስምምነት ሙሉ በሙሉ ጥሷል በማለት ማምሻውን ባወጣው መግለጫ ወንጅሏል።

የሕወሃት መግለጫ፣ የትግራይ ሕዝብ እና ሕወሃት ዳግም የሚቀሰቀስ ጦርነት በሁለቱም ወገኖች ላይ ከፍተኛ ውድመት እንደሚያደርስ በመግለጽ፣ የፌደራል መንግሥቱ ባለስልጣናት የግጭት ማቆም ስምምነቱን ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ በማድረግ የሰላም መንገድን እንዲከተሉ ሲጠይቁ ቆይተዋል ብሏል።

የአፋር ክልላዊ መንግሥት ባለስልጣናት ላለፉ ጥፋቶቻቸው በመጸጸት ፋንታ ፌደራል መንግሥቱ ላደራጀው ጸረ-ትግራይ ታጣቂ ቡድን ነጻ መሬት በመፍቀድ፣ የሌላ ዙር ጦርነት ማስፈጸሚያ መሳሪያ እየሆኑ ይገኛሉ የሚል ክስም ሕወሃት አቅርቧል።

የፌደራል መንግስት በጉዳዩ ላይ እስካሁን ያለው ነገር የለም