ሱፐር ደብል ቲ ያሰራቸው እና ያሳሰራቸው የቀድሞ ሰራተኞች በስም እና ምስል እየተለዩ ነው

ሱፐር ደብል ቲ ያሰራቸው እና ያሳሰራቸው የቀድሞ ሰራተኞች በስም እና ምስል እየተለዩ ነው፣ ያሉበትን ያላወቀ ቤተሰብ ካለ እዚህ ነን እያሉ ነው፣ እነማን ናቸው?

– ድርጅቱ ሰራተኞች ላይ የሚፈፅመው በደል እና ወንጀል ሚድያ ላይ መውጣቱን ተከትሎ በቅጥር ግቢ ውስጥ ከ5 ሺህ በላይ የሚሆኑ ሰራተኞች ስልካቸው በየቀኑ እየተፈተሸ መሆኑ ታውቋል

– የቀድሞ ሰራተኞች የሆኑት እስር ላይ የሚገኘው ወጣት ጉታታ እና ክፉኛ ተደብድቦ ለነርቭ መጎዳት የተዳረገው ወጣት መንክርን ዝርዝር ታሪክ ይዘናል

– ዳለቲ ላይ 42፣ ፉሪ 17 እንዲሁም ገላን ጉዳ ካንተሪ 13 የቀድሞ የድርጅቱ ሰራተኞች ታስረው ይገኛሉ፣ እስር ቤት ሆነው ድረሱልን እያሉ ያሰሙት መልዕክት ተካቷል

– የታሳሪዎቹን ስም እና ፎቶ በከፊል አሰባስበናል፣ በርካቶች በፍርሀት ተበታትነው በሀገሪቱ ዙርያ ተሸሽገው እንደሚገኙ ለሚድያችን እያሳወቁ ነው

– በዊልቼር ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የተገኘው ተደብዳቢው ወጣት መንክር ህክምና ላይ የነበረ ሳይሆን ከአዳማ ከተማ ከፀበል ቦታ ተወስዶ ጋዜጠኞቹ ጋር እንዲናገር መወሰዱ ታውቋል

– አዲስ አበባ ውስጥ ለመንክር ባሳለፍነው ቅዳሜ ዊልቼር በመኪና ተጭኖ ሲወሰድለት የሚያሳይ ምስል ደርሶናል፣ ከጋዜጣ መግለጫው በኋላ ወጣት መንክር ወደ መቄዶንያ መወሰዱም ታውቋል

– የዛሬ ሳምንት ወደ ድርጅቱ ተጋብዘው የሄዱ ጋዜጠኞች በባንክ አካውንታቸው ይገባላችኋል የተባለውን አበል እንደተከለከሉ ለሚድያችን ጠቁመዋል

ለሁሉም ክፍት ሆኖ የቀረበውን ይህን ዘገባ ያንብቡ:
https://tinyurl.com/2wyybr9e