የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የዓለም የምግብ ፕሮግራም በመጪዎቹ አምስት ዓመታት፣ በኢትዮጵያ ለሚያከናውናቸው የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦትና አገልግሎቶች፣ ከግማሽ ትሪሊዮን ብር በላይ ሊያስፈልገው እንደሚችል፣ በውይይት ላይ በሚገኘው በድርጅቱ ስትራቴጂካዊ ረቂቅ ሰነድ ተመላከተ፡፡
ሪፖርተር የተመለከተው ረቂቅ ሰነድ የዓለም የምግብ ፕሮግራም የሥራ አመራር ቦርድ፣ በመጪው ሳምንት በሚያደርገው መደበኛ ስብሰባ ውይይት እንደሚካሄድበት ይገልጻል፡፡
ለአምስት ዓመት ስትራቴጂካዊ ዕቅድ ያስፈልጋል ተብሎ የታሰበው 3.3 ቢሊዮን ዶላር ወይም 505.5 ቢሊዮን ብር አካባቢ ነው፡፡ ሰነዱ በኢትዮጵያ 129.7 ሚሊዮን ሕዝብ ዝቅተኛ ገቢ ያለው መሆኑንና አገሪቱ ከ193 አገሮች በድህነት 180ኛ ደረጃ የያዘች መሆኗን ያስረዳል፡፡ https://ethiopianreporter.com/147634/