መንግሥት በኦሞ ስኳር ፋብሪካ ግንባታ የተፈጸሙ የመብት ጥሰቶችን በሦስት ወራት ይፋ እንዲያደርግ ተጠየቀ

የአፍሪካ የሰዎችና የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን፣ መንግሥት በኦሞ ስኳር ፋብሪካ ግንባታ ወቅት ተፈጽመዋል የተባሉ የመብት ጥሰቶችን ጥናት አድርጎ በሦስት ወራት ይፋ እንዲያደርግ ጠየቀ፡፡

ኮሚሽኑ ጥቅምት 26 ቀን 2018 ዓ.ም. ይፋ ባደረገው ባለ 60 ገጽ ሪፖርት፣ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የታችኛው ኦሞ ወንዝ በሚገኙ የአካባቢው ነዋሪዎች ከስኳር ፋብሪካው ግንባታ ጋር በተገናኘ መብቶች ተጥሰዋል ሲል አስታውቋል፡፡

የመብት ተቋሙ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት የኦሞ ኩራዝ ፕሮጀክት ግንባታ የአካባቢ፣ የማኅበራዊና ሰብዓዊ መብቶች ጥናት እንዲያካሂድ፣ ከዚህ ቀደም ጥናት አካሂዶ ከነበረ ደግሞ ጥናቱን ለሕዝብ ይፋ እንዲያደርግ ጠይቋል፡፡ https://ethiopianreporter.com/147631/