አመራሮች በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂዎች ጥቃት ተገደሉ

በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ያያ ጉለሌ ወረዳ የብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ክንፉ ነጋሹን ጨምሮ አራት የቀበሌ አመራሮች አሊዴራ በተባለ ቀበሌ ቅዳሜ’ለት በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂዎች ጥቃት እንደተገደሉ ዋዜማ ሠምታለች። በጥቃቱ፣ ለጊዜው ቁጥራቸው ያልታወቀ በርካታ የመከላከያ፣ የፖሊስና የሚሊሺያ አባላት ጭምር እንደተገደሉ ምንጮች ነግረውናል። ታጣቂዎቹ፣ ሦስት የቀበሌ አመራሮችን አፍነው መወሰዳቸውንም ምንጮች ገልጸዋል። ታጣቂዎቹ ከምንጊዜውም በበለጠ ቁጥራቸው ከፍተኛ ነበር ተብሏል።