የድሬደዋ ፖሊስ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂዎች ገብተው እንደነበር አስታውቋል።

የድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን፣ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂዎች ወደ ድሬደዋ አሥተዳደር፣ ምዕራብ ሐረርጌ ዞን እና ሶማሌ ክልል ገብተው እንደነበር አስታውቋል። ፖሊስ ከቡድኑ ጀርባ የነበሩ 34 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን መግለጡን የዘገበው የድሬዳዋ አስተዳደር ቴሌቪዥን ነው። ጸጥታ ኃይሎች ሰሞኑን በወሰዱት ርምጃ 43 ታጣቂዎች መገደላቸውንም ጣቢያው ጠቅሷል። ቡድኑ፣ በአሥተዳደሩና በአጎራባች ክልሎች፣ በመሠረተ ልማቶችና ኢንዱስትሪዎች ላይ ጥቃት ለማድረስ እና የብሔር ግጭት ለመቀስቀስ ተዘጋጅቶ ነበር ተብሏል።