ኢትዮጵያ በሕግ የበላይነት ምዘና ከ143 የዓለም አገራት 132ኛ ደረጃ ላይ ተቀመጠች።

ኢትዮጵያ በሕግ የበላይነት ምዘና ከ143 የዓለም አገራት 132ኛ ደረጃ ላይ ተቀመጠች። ከ34 የአፍሪካ አገራት መካከል ደሞ ኢትዮጵያ አራት አገራትን ብቻ በመብለጥ 30ኛ ደረጃ አግኝታለች። ዓለማቀፉ የፍትሕ ፕሮጀክት ባወጣው ሪፖርት፣ በተያዘው የአውሮፓዊያን ዓመት የኢትዮጵያ የሕግ የበላይነት ደረጃ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር በ2 ነጥብ 4 በመቶ ቀንሷል ብሏል። ዝቅተኛ ገቢ ካላቸው 16 አገራት መካከል ደሞ፣ ኢትዮጵያ 13ኛ ደረጃ ነው ያገኘችው። በአገሪቱ ለ5 ተከታታይ ዓመታት ተቋማት እየተዳከሙ፣ የሲቪክ ምኅዳሩ እየጠበበና የፖለቲካ ጣልቃ ገብነት እየጨመረ መሄዱንም ሪፖርቱ ጠቅሷል። ኢትዮጵያ፣ በተለይ ሃሳብን በነጻነት በመግለጽ፣ በመሰብሰብ ነጻነት እና በሲቪክ ተሳትፎ መስኮች እጅግ ዝቅተኛውን ውጤት አስመዝግባለች።