የልጅ እያሱ ኮር አሃዶች በጥምረት በርካታ የጠላት ሃይል በመደምሰስ ታላቅ ድል ተጎናፀፉ::

የልጅ እያሱ ኮር አሃዶች በጥምረት በርካታ የጠላት ሃይል በመደምሰስ ከ30 በላይ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት እና 45 ክላሽ በመማረክ ታላቅ ድል ተጎናፀፉ::

የልጅ እያሱ ኮር ጥቅምት 8/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ  11:00 እስከ ቀኑ 5:00 ሰዓት በሰሜን ወሎ ዞን ሀብሩ ወረዳ በውርጌሳ አካባቢ አምባሰል ወረዳ ውጫሌ ጨፌ አና ወርቃረያ እስከ ኩታ በር ወረዳ ተጋድሎ በማድረግ ታላቅ ድል አስመዘገበ::

በዚህ የውጊያ ግንባር በሰሜን ወሎ ዞን ሀብሩ ወረዳ ውርጌሳ እና አካባቢው በራስ አሊ ክፍለ ጦር ስር የምትገኘው አራተኛ ሻለቃ እና በራምቦ ክፍለ ጦር ስር የሚገኙት ሻለቃ አንድ እና ሻለቃ ሁለት በመሆን በውርጌሳ እና አካባቢው ያሉትን ተራሮች ተብትቦ ይዞ የነበረውን የ11ኛ እዝ አካላት ላይ በተደረገ የማጥቃት እርምጃ ገሚሱ ሲገደል ገሚሱ ደግሞ እጅ ሰጥቷል።
የአካባቢው ነዋሪ አንዳሉት በተደረገው ውጊያ መከላከያ ላይ ከፍተኛ ኪሳራ እንደደረሰበት የአይን ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል።

በዚህ ግንባር ብቻ የሞተ የጥላት ወታደር በርካታ ሲሆን ምርኮኛ 30 የተማረከ ክላሽ ብዛት 45 የወገብ ትጥቅ 42  ቦንብ 74 የብሬን ተተኳሽ 1417 የክላሽ ተተኳሽ 3375 የመገናኛ ሬድዮ 1 የዝናብ ልብስ/Rain coat/ 27 በመማረክ ውጊያው ተቋጭቷል።

ሁለተኛው ግንባር ውጫሌ ከተማ ላይ የነበረ ሲሆን የአምባሰል ወረዳ ዋና መቀመጫ የሆነችው ውጫሌ ላይ ወፍ ሲበር ጭምር ሲደነብር ውሎ የሚያድረው እና ከተማውን ለመያዝ በተደረገ የተኩስ ልውውጥ በልጅ እያሱ ኮር አመራሩን የተነጠቀው ዝክንትል ወታደር ነፍስ ግቢ ነፍስ ውጭ አይነት ውሎ እንደዋለ እና ብዙ የሰራዊቱ አባል በፋኖ ጥይት ሰለባ እንደሆነ የውጫሌ ነዋሪ እና የራስ አሊ ክፍለ ጦር አካል የሆነችው ሁለተኛ ሻለቃ ተዋጊዎች የውጊያ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል።

ሶስተኛው ግንባር ከአምባሰል ወረዳ እስከ ኩታበር የተዘረጋው ግንባር ሲሆን ከ ሀይቅ አቅጣጫ የውጫሌውን የጥላት ኃይል ለማገዝ እና ማርዬ ለመግባት የመጣውን የመከላከያ ኮማንዶ ጦር የቤተ አማራ ክፍለ ጦር ፋሲል ሻለቃ ከቤተ አማራ ክፍለ ጦር ቃኝ ጋር  በመሆን ወደ ውጫሌ ለመሄድ ያሰበውን የጥላት ጦር ጨፌ ላይ አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ከሀያ በላይ ቁስለኛ፣ ከ15በላይ ሙት ይዞ ሀይቅ ሲገባ ከደሴ በኩታ በር አድርጎ ወደ ማርዬ ለመግባት ያሰበው የጥላት ጦር ወርቃርያ ላይ በራምቦ ክፍለ ጦር አራተኛ ሻለቃ ተመክቶ ተመልሷል።

በተደረገው ውጊያ በጉባላፍቶ ወረዳ ሀራ ከተማ ተፀንሶ እዛው ሀራ ከተማ የተወለደውን የመከላከያ ሰራዊት 11ኛ እዝ ዳዴ እንኳን ብሎ ሳይጨርስ ሀብሩ እና አምባሰል ራያ እና የጁ ቅርጥፍ አድርገው መብላት የለመዱት የምኒልክ ልጆች አሁንም የልማዳቸውን በመወጣት የጥላትን ጦር ዶግ አመድ እያደረጉት ይገኛሉ።

በተለይ ሰሞኑን የአማራን ህዝብ አንገት ለማስደፋት በማሰብ እና ትግሉ በሰራዊት መክዳት እና መማረክ ከፍተኛ ኪሳራ ውስጥ የገባው መንግስት የፋኖን የትግል ሀዲድ ለማሳት እና የተማረኩ ሰራዊት ላይ እርምጃ እንድወሰድባቸው መገፋፋትን መሰረት ያደረገ የጭካኔ በትር በእህቶቻችን ላይ ቢያሳርፍም እኛ አማራዎች የአያት ቅድመ አያቶቻችን ልጆች ስለሆን ወደ ግራም ይሁን ወደ ቀኝ አንድም ኢንች ዝንፍ ሳንል ለተነሳንለት አላማ ከተለምነው ትልም ላይ እንገኛለን።

ስለሆነም የማረክነውን አለም ዓቀፋ የምርኮ ህግ በሚፈቅደው መሰረት በመያዝ የመንግስትን ምኞት ከንቱ በማድረግ ትግላችንን አጠናክረን አየቀጠልን እንደሆን የዛሬው የምርኮ አያያዛችን ወታደራዊ ስነ ምግባራችን ምን ያክል የተገራ እንደሆነ ማሳያ ነው።

መፅሐፍ ንጉስ በወታደሩ ብዛት አይድንም ይላልና የብልፅግና ስርዓትም ላይ እየሆነ ያለው መፅሐፋ በሚለው ልክ ስለሆነ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ሚሊሻ አድማ ብተና እና ፖሊስ አማራ ላይ የሚደረገውን የግፍ ግፍ ተመልክታችሁ ፋኖን እንድትቀላቀሉ ስንል የተለመደ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

በአፋብኃ ሚኒሊክ ዕዝ እልጅ እያሱ ኮር ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ!