የ19 ዓመቷ ፋኒት በዓለም ዋሴ የግፍ ግድያ የጦር ወንጀል ነው

የ19 ዓመቷ ፋኒት በዓለም ዋሴ የግፍ ግድያ የጦር ወንጀል ነው፤
መንግስት መሆን ያቃተው ብልጽግና የአማጽነት ወግም እርቆታል፤ Yared Hailemariam
++++
A young woman with short curly hair wearing a plaid shirt and necklace stands outdoors under a blue sky with white clouds a white dove flies above her two lit candles positioned at the bottom foreground በአለም አቀፍ የሰብአዊነት ህግ (International Humanitarian Law) ወይም the laws of armed conflict እና የGeneva Convention በመባል በሚታወቁት አለም አቀፍ ሕጎች የጦርነትን ሁኔታና በጦርነት ወቅት ቆስለው ወይም ሳይቆስሉ የሚማረኩ የተቀናቃኝ ጦር አባላትን አያያዝ የሚደነግጉ አንቀጾች አሉ፡፡ በእነዚህ ድንጋጌዎች መሠረት Hors de combat (out of the fight) የሚባሉት ከተፋላሚዎቹ ሃይሎች መካከል በጦርነቱ ጉዳት ደርሶባቸው የቆሰሉና የተማረኩ፣ በሕመም ላይ የሚገኙ ወይም እጅ ሰጥተው በተቀናቃኝ ጦር የተማረኩ ሰዎች እና Prisoners of war (POWs) የጦር እስረኞች ምን አይነት የሕግ ጥበቃ ሊደረግላቸው እንደሚገባና ጥበቃ ማድረግ በሚገባቸው አካላት ላይ ስለተጣለው ሃላፊነት እነዚህ ህጎች በዝርዝር ይደነግጋሉ፡፡ በጉዳት ምክንያት ወይም በምርኮ የተያዘ ሰው ተገቢው ህክምና እና ጥበቃ ተደርጎላቸው ሰብአዊነት በተሞላው አያያዝ እንዲቆዩ መደረግ እንዳለበት ይደነግጋሉ፡፡ ይህን መጣስ እንደ ጦር ወንጀል እንደሚቆጠርም እነዚህ ሕጎች ይገልጻሉ፡፡
ከእነዚህ መሠረታዊና ቁልፍ ከሆኑ የጦርነት መርሆዎች በእንግሊዘኛው ፤
1ኛ/ IHL prohibits the use of unnecessary force and weapons that cause unnecessary suffering. This includes prohibiting torture, cruel treatment, and the use of excessive force. (የአለም አቀፉ የሰብአዊነት ሕግ አላስፈላጊ እና ያልተመጣጠነ ሃይል እና መሳሪያ በመጠቀም በተማረኩ፣ ቆስለው በተያዙና የጦር እስረኛ በሆኑ ሰዎች ላይ መጠቀም፣ የማሰቃየት ወይም ጭካኔ የተሞላው አያያዝ መፈጸም የተከለከለ መሆኑን ይደነግጋል)
2ኛ/ All combatants, including enemy combatants, must be treated with humanity and dignity. They cannot be subjected to cruel or inhumane treatment, and their cultural and religious practices must be respected. (ሁሉም በጦርነት ወቅት የሚማረኩ ሰዎች የጠላት ጦርን ጨምሮ በተያዙ ጊዜ ሰብአዊነት በተሞላው እና ለሰው ልጅ የሚገባው ክብር ሳይነፈጋቸው መቆየት እንዳለባቸው፤ ከማናቸውም ለሰው ልጅ የማይገባ አያያዝ፣ ባህላቸውን እና እምነታቸውን ከሚጻረር አድራጎት መጠበቅ እንዳለባቸውም ይደነግጋል፡፡
የጦር ሕግ የማይገዛው ብልጽግና በትግራይ የፈጸመውን የጦር ወንጀል በአማራም ክልል በብዙ መልኩ እየፈጸመው ነው፡፡ ባለፉት ሁለት አመታት በአማራ ክልል በድሮን ጥቃት የአገዛዝ ሥርአቱ ሰራዊቶች የጨፈጨፏቸው ንጹሃን ዜጎችና ህጻናት የሥርአቱ የጦር ወንጀል ሰለባዎች ናቸው፡፡ ዛሬ እየሰማን ያለነው የ19 ዓመቷ ፋኒት በዓለም ዋሴ አሰቃቂ ግድያም እንዲሁ የብልጽና መንግስት አለም አቀፍ ሕግ የማይገዛው ነውረኛና የጦር ወንጀል በመፈጸም ሕዝብን የማሸበርን ተግባርን ዋነኛ ስልቱ አድርጎ መቀጠሉን ማሳያ ነው፡፡ እንዴት አንድ በመንግስት ሥር የሚመራ ወታደራዊ አካል በምርኮ የያዛትን፣ ሊያውም የአገሩን ልጅ፣ ሊያው የ19 አመት ታዳጊ ወጣት ሴት በተገለጸው መልኩ ጡቷን ቆርጦና ቆዳዋን ገፎ በአሰቃቂ ሁኔታ ከገደለ በኋላ ሕዝብ አስከሬኗን እንዲያይና እንዲሸበር እከተማ መሃል አደባባይ ላይ ይጥላል?
መንግስት ጽንፈኛ እያለ የሚያራክሳቸው የፋኖ ታጣቂዎች በመቶዎች የሚቆጠሩ ምርኮኛ ያደረጓቸውን የመንግስት ወታደሮች በእንክብካቤ ይዘው ለአለም አቀፍ ቀይመስቀል ሲያስረክቡ የአለም አቀፍ ስምምነቶችን የፈረመችውን አገር የሚወክለው የመንግስት ሠራዊት ግን አንዲት የቆሰለች የ19 አመት ታዳጊ ወጣት ወታደር ይዞ በዚህ መልኩ አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ መግደል መንግስት መሆን የተሳነው ብልጽግና የአማጺዎችን ያህል እንኳ የአለም አቀፍ ሕጎችን ለማክበር እና ለመረዳት የሚያስችል ሥልጡን ባህሪ ያጣ መሆኑን ነው ያሳየው፡፡
የፖለቲካ እስረኞችንም እንዲሁ በተመሳሳይ ሁኔታ ለስቃይ መዳረግ የአገዛዝ ስርአቱ ሕዝብን የማሸበሪያ ስልት አድርጎ መውሰዱን በእስር ላይ የሚገኙት የህሊና እና ፖለቲካ እስረኞች ሁኔታ ጥሩ ማሳያ ነው፡፡ በቃሊቲና በቅሊንጦ እስር ቤቶች የሚገኙ ታዋቂ የፖለቲካ እስረኞች ድብደባ፣ እንግልትና ወከባ እንደሚፈጸምባቸው፣ ህክምና እንደሚከለከሉ፣ በቤተሰቦቻቸውም እንዳይጎበኙ መደረጉን እና ጠበቆቻቸውም ዛቻና ማስፈራሪያ እየደረሰባቸው መሆኑን ሰሞኑን ተደጋግሞ እየሰማን ነው፡፡ የብልጽግና ሰዎች ፍርሃትና ስጋታቸው በጨመረ ቁጥር አስከፊ የሆኑ የመብት ጥሰቶችን መፈጸመና ህዝብን ማሸበርን እንደ ስልት ተያይዘውታል፡፡ ሲያልቅ አያምር ነው ነገሩ፡፡
ቢዘገይም ግን ፍርዱ አይቀርም!