በየዓመቱ የሚከበረው የኢትዮጵያ ፌስቲቫል በአሌክሳንደሪያ፣ ቨርጂኒያ በዛሬው ዕለት በድምቀት ተከበረ። ከስፍራው በደረሰን ሪፖርት መሰረት በርካታ ቁጥር ያላቸው ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ዝናቡንና ንፋሱን ተቋቁመው በዝግጅቱ ላይ ታድመው ነበር። በተለይም አሜሪካ ውስጥ ተወልደው ያደጉ ወጣቶች የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ በታላቅ ክብር ሲዘክሩ በአንጻሩ ደግሞ የአብይ አህመድ/አሮሙማ አገዛዝ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ላለፉት 7 ዓመታት ሲያረክስና ሲያቆሽሽ እንዲሁም በማንኛውም በዓላት ላይ ህዝብ ይዞ እንዳይወጣ ከመከልከሉም በላይ ከአልባሳትና ከቤተክርስቲያናት ንዋየ ቅዳሳት ጭምር ሲፍቅ ቆይቶ ጭራሹን በሌላ ሊቀይረው እንደሆነ እያስወራ ነው። ሆኖም የባዕዳን ተላላኪና ቅጥረኛ የሆነው ብልፅግና ፓርቲ በሚሊዮኖች መስዋዕትነት የታነጸውንና በመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ልብ ውስጥ የተቀረጸውን የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ በምንም ዓይነት ሁኔታ ከህዝብ ህሊና ሊነጥል እንደማይችል ይታወቃል። በተለይም የዛሬውን የወጣቶች የሰንደቅ ዓላማ መዘከርና ፍቅራቸውን ማሳየት አብይ አህመድ ሲሰማ “አማራ ፋኖ መጣብኝ” ብሎ እንደሚያራዠውና እንቅልፍ እንደሚነሳው አይጠረጠርም።