ቅዳሜና እሁድ ከሚከበረው ኢሬቻ በዓል ጋር በተያያዘ፣ ቀለሙ ጥቁር፣ ቀይ እና ነጭ የኾነውን “የአባ ገዳ” ባንዲራ በተሽከርካሪዎቻቸው ላይ ያላሠሩ አሽከርካሪዎች 2 ሺሕ ብር እየተቀጡ መኾኑን መረጃኮም ሰምቷል።
የገንዘብ ቅጣቱ በሸገር ከተማ ኹሉም ክፍለ ከተሞች ተፈጻሚ እየተደረገ መኾኑን ያነጋገርናቸው አሽከርካሪዎች ነግረውናል።
ከተለያዩ የክልሉ ከተሞች ወደ አዲስ አበባ የሚገቡ ባንዲራውን ያላሠሩ ተሽከርካሪዎችም የገንዘብ ቅጣት እንደሚጣልባቸው ምንጮች አስረድተዋል።
ቅጣቱን የሚጥሉት፣ የሸገር ከተማ አስተዳደር የትራፊክ ፖሊስ አባላት ናቸው ተብሏል። ሆቴሎች፣ ባንኮች፣ የንግድ መደብሮችና የመንግሥት መስሪያ ቤቶችም ይህንኑ ባንዲራ እንዲያውለበልቡ እንደታዘዙ ሠምተናል።