አባ ፋኑኤል በግላቸው ከሚፈጽሙት በደል ተጨማሪ ሌሎችንም ታደሰ ሲሳይና ኤወስጣጤዎስ የመሳሰሉት ዝሙተኞን በመሸፈን፣ በመደገፍና በመተባበር ተደጋጋሚ በቤተክርስቲያን ላይ ወንጀል፣ ጥፋትና ኃጢአት ሲፈጽሙ ኖረዋል፡፡ በአገር ውስጥም ህዝበ ክርስቲያኑን እያስፈጁ በዝሙት፣ በዘረኝነት፣ በገንዘብ ዝርፊያና በተለያዩ አስነዋሪ ተግባሮች ላይ የተጠመዱ ብዙ የአቡነ ፋኑኤል ብጤዎች አሉ።
ጳጳሳቱ የተበላሸ ተግባራቸውን አርመው ለሚቃጠሉት አብያተ ክርስቲያናትና ለሚታረዱት ክርስቲያኖች ምስክር እንዲሆኑ ሲነገራቸው አይሰሙም፡፡ “ቅዱስ ሲኖዶስ” በሚባለው ስም ራሳቸውን ጋርደው ተግባራቸው ለራሳቸው ገንዘብ መጨመር ብቻ ነው፡፡ የነሱ ስሕተት ሲነገራቸው ቤተ ክርስቲያን እንደተሰደበች አድርገው ለካኗቸው ቄሶች ይናገራሉ፡፡ እነሱ የካኗቸው ቄሶችም የሚሰሙት የካኗቸውን ጳጳሳት ነው፡፡ ቀኖናውን አያውቁትም አልተማሩትም፡፡ የሚሰብኩት ስለካኗቸው ጳጳሳት ቅድስና የበቁ እንደሆነ እያሰመሰሉ ነው፡፡በገንዘብ ጵጵስናውን የገዙትና ቅስናውን በገንዘብ እየገዙ የተካኑት ቄሶች እርስ በርሳቸው የሚወዳደሱ ለህዝብ ለቤተ ክርስቲያን ክብር ያልቆሙ መሆናቸውን ሁሉም ያውቃል፡፡
ከማያነቡት አሮጊት እናቶች በቀር የቀሲስ አስተራየን ጽሑፍና ንግግር የሰማውን ሁሉ አሁን የጥምር ቄሶች ንቅናቄ አነቃቅቶታል ፡፡ቀስቅሶታል፡፡ በድፍረት እየወጡ የሚናገሩ ክርስቲያኖች ወደፊት መጥተዋል፡፡ እነዚሁ እነ አባ ፋኑኤልና የመሳሰሉ ጳጳሳትና በነሱ የተካኑት ቄሶች እንቅስቃሴው እንዳይቀጥል የተለያየ ተንኮል በመጎንጎን ላይ መሆናቸው ይታወቃል፡፡ ይህን ተገንዝበውና ለንቅናቄው ተግባር መሳካት ይጠቅማሉ ብለው ዶክተር መኮንን ባይሴ ያሰባሰቧቸውን የቀሲስ አስተርአየን ጽሑፎች ከነሊንካቸው አያይዘው አቅርብውልናል። ዶክተር መኮንን ያቀረቡልንን በትኩረት አንብባችሁ እንቅስቃሴውን የምትመሩት ቄሶች እንድተበረቱ፣ እንዲሁም ሕዝበ ክርስቲያኑም ነቅቶ እንቅስቃሴውን እንዲከታተልና ድጋፍ በመስጠት ከግቡ እንዲደርስ በመረጃና ማስረጃ መታጠቅ አስፈላጊ ስለሆነ አቅርበንላችኋል። ጥምረት ለቤተ ክርስቲያን ዓለም አቀፍ የካህናትና ምእመናን ጥያቄና ማሳሰቢያ