ጥብቅ ወታደራዊ መረጃ!
በእግረኛ ሰራዊቱ ተስፋ የቆረጠው የዐብይ አህመድ አገዛዝ ሰው ከልባ አውሮፕላንን በመጠቀም በተመሣሣይ ሰዓት በተለያዩ ቦታዎች ላይ ጥቃት ለመፈፀም መዘጋጀቱ ተሰምቷል።
ጥቃቱ ይፈፀማል የተባለው ጨለማን ተገን በማድረግ ሲሆን፡ ጥቃት ይፈፀምባቸዋል የተባሉ አከባቢዎች ተለይተዋል ሲሉ የመረብ ሚዲያ ወታደራዊ ምንጮች ገልፀዋል።
ጥቃቱ የሚፈፀመው የፋኖ ጦር ቤዝ ተብለው በተለዩ ቀጠናዎችና የፋኖ አመራሮች በስፋት ይገኙባቸዋል በተባሉ ቦታዎች ላይ ነው።
የመረብ ሚዲያ ወታደራዊ ምንጭ እንደገለፁት፡ ጥቃቱ የሚፈፀመው በተመሳሳይ ሰዓት በተለያዩ ቦታዎች ላይ ነው ያሉ ሲሆን፡ ለዚህም ሰው አልባ አውሮፕላኖች ተዘጋጅተዋል ብለዋል።
ጥቃቱ የሚፈፀመው ጨለማን ተገን በማድረግ(አጥቢያ ለሊት ላይ) ነው የሚሉት ምንጫችን፡ ኦፕሬሽኑ የሚመራው አዲስ አበባ መገናኛ አከባቢ በሚገኝ የወታደራዊ ደህንነት ቢሮ ነው ሲሉ ለጣቢያችን ተናግረዋል።
ጥቃቱ ዛሬ መስከረም 21/2018 ዓ/ም አጥቢያ ለሊቱን ወይም በቀጣዮቹ ቀናት ሊፈፀም ይችላል ተብሏል።
ስለሆነም፡ ሕዝቡ በቂ ጥንቃቄ እንዲያደርግ መልዕክት ያስተላለፉት ምንጫችን፡ በተለይ የፋኖ አመራሮችና አባላት ለጥቃት ከሚያጋልጡ እንቅስቃሴዎች እንዲቆጠቡ አሳበዋል።