የትግል ስልት በጠላት አይመረጥም
ትግል ጠላት ምን ይለኛል ተብሎ እንደማይደረግ ሁሉ ስልቱንም ከጠላት መጠበቅ አይቻለም
=========================================
ትግል ሲታሰብ ታጋዩ የመታገያ ምክኛቶቹ በስኬት እንዲቋጩ የመታገያ ስልቶች ከወዲሁ ይቀይሳል፡፡ ስልቶቹ የአጭር እና የረጅም ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ በየግዜው እንደ ሁኔታ ለውጥ የሚቀየሱ ስልቶች ግዜን እና የጠላትን ጥንካሬ ማለፊያ እና ማዳከሚያ ናቸው፡፡ እረጅሙ የትግል ስልት ግን በጠላት በኩል ወይንም አለማቀፋዊ እና ሐገራዊ ሁኔታ እስካልተቀየረ እስከድል የሚቀጥል ስልት ነው፡፡ ለምሳሌ የመሳርያ ትግል ምርጫው የሆነው ባለው ሁኔታ ተገዶ መሳርያ እንዲያነሳ የተገደደ ትግል በመሆኑ ስለሆነ የመሳሪያ አፈሙዝ የሚዘቀዘቀው ከድል በኋላ ነው፡፡ ወይንም ትግሉ የታሰበለትን አላማ ሲያሟላ ብቻ ነው፡፡
የፋኖን ትግል በዚህ ልናይ እንችላለን፡፡ በሐገራችን የሰፈነው ዘር ተኮር ፖለቲካ መሰረቱ ጸረ አማራ እና ጸረ ኢትዮጵያ ነው፡፡ የስርአቱ አቀንቃኞች አማራን ማጥፋት ኢምፔሪያል ኢትዮጵያን ማዳከም እና የተከፋፈሉ ትንንሽ ሀገራት መመስረት ነበር ባብዛኛው አሟልተዋል፡፡ በጠላትነት የፈረጁትን ሕዝብም እስካሁን የጥፋት ጦርነት ከፍተው እየገደሉት፤ እያፈናቀሉት እና በሐገሩ ስደተኛ እያረጉት ነው፡፡
ይህ ሁኔታ የወረደበት የዚህ ትውልድ የአማራ ወጣት ወዶ ሳይሆን ተገዶ መሳርያ አንስቷል ይህ መሳርያ እስከ ድል ይቀጥላል፡፡ ትውልዱ የተነሱበትን ጠላቶቹን ለመመከት ብሎም ለማቸነፍ የአጭር እና እረጅም ስልቶቹን በስራ ያውላል፡፡ ይህ ሲሆን መታገያ ስልቱን ጠላት ሊወስንለት አይችልም፡፡ ጠላት አናጥሎ ሊያጠፋው ስለሆነ አላማው በአጭር የትግል ስልቶች በተለያየ ግዜ ለግዜው በሚመጥኑ ስልቶችን በመጠቀም ጠላትን ይታገላል ትግሉን ከግብ ያደርሳል፡፡
ትብብር አስፈላጉ ሆኖ ሲገኝ ትብብሩን ለፋኖ ታጋዮች የሚመርጥለት የአብይ የፕሮፖጋንዳ ሰራዊት እንዳልሆነ ሊታወቅም ይገባል ወይንም እቤቱ የተቀመጠ ከትግሉ ሜዳ የሌለ ሰው አይሆንም ምክኛቱ ደግሞ ስለትግሉ እና በትግሉ አካሄድ ስለአሉት ሁኔታወች ስለማያውቅ ማለት ነው፡፡ ጠላት ምንግዜም ጠላት ነው እኔ እንጅ አንተ ከነእከሌ ጋር መተባበር አትችልም ሊል አይችልም ምናገባው እናስ ስለትግሉ ሞራል ወሳኝ ይሆናል እሱ ጠላት ነው ከጠላት ጥሩ የሚጠብቁ ካሉ ጅሎች ወይንም ልቦናቸው ከወዲያ አካላቸው እዚህ ያሉ የጠላት ሰላዮች ናቸው፡፡
ባጭሩ የሰሞኑ በሰሜን ወሎ የታየ ጀግንነት በጠላት ጎራ ሽብር ከፍቷል ወዳጅ ነን ይሉ የነበሩት ሀሰተኞችን ጭምር አስበርግጓል እናም ከነ እንቶኔ ስለወገነ ነው ይህ የሆነው የሚሉ ጅሎች የትግል አካሄድን የማያውቁ አለያ ሰርጎ ገብ ጣላት አፍቃሪወች ናቸው፡፡ ትግሉ አንድ ምእራፍ እየተሻገረ በመሆኑ ጥራትም እያገኘ ይሄዳል፡፡ እኛም የዚህን ትግል ግብ መምታት የምንመኝ እና ለግማሽ ምእተ አመት የተንሰራፋው ዘረኝነት ተወግዶ ሐገራችን ወደነበረችበት እንድትመለስ በጸሎትም በመንፈስም እንራዳለን አይዟችሁ በርቱ እንላለን፡፡ ( ዶክተር መንግስቱ ሙሴ እንደጻፈው )