ከአውሮፓዊያኑ 2016 እስከ 2024 ባሉት ዓመታት ኢትዮጵያ ኢንተርኔት በመዘጋት ከአፍሪካ የቀዳሚነት ደረጃ መያዟን “ኢንተርኔት ሸትዳውን ኢን አፍሪካ” የተሠኘ ጥናት አመልክቷል።
በአሕጉር ደረጃ በተጠቀሠው ጊዜ 190 ያህል የኢንተርኔት መዘጋት ክስተቶች እንደተመዘገቡ የጠቀሠው ጥናቱ፣ ኢትዮጵያ በዚህ ጊዜ ውስጥ 30 ጊዜ ኢንተርኔት ማቋረጧን ገልጧል።
የኢንተርኔት መቋረጥ በኢትዮጵያ በሰብዓዊ መብቶች ላይ ተጽዕኖ እንደሚፈጥርም ጥናቱ አመልክቷል።
21 ጊዜ ኢንተርኔትን በመዝጋት ሁለተኛ ደረጃ የያዘችው ሱዳን ስትኾን፣ በሦስተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠችው አልጀሪያ ናት። በ2016 ዓ፣ም በአሕጉር ደረጃ 14 የነበረው የኢንተርኔት መዘጋት ብዛት፣ በ2024 ዓ፣ም ወደ 28 ጨምሮ እንደነበር በጥናቱ ላይ ተጠቅሷል።