2ተኛ ቀን ዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው) በታላቅ ድል ታጅቦ እንደቀጠለ ነው።

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ መስከረም 14 ቀን 2018 ዓ.ም ከጧቱ 12:00 ሰዓት የተጀመረው ዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው) በአምስቱም ኮሮች እና በዕዙ ልዩ ዘመቻ ከፍተኛ ተጋድሎ በማድረግ አስደናቂ ድሎችን እያስመዘገበ ተጠናክሮ ቀጥሏል።
2ተኛ ቀኑን በያዘው “ዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው) በዛሬው ዕለት መስከረም 15 ቀን 2018 ዓ.ም ተጠንክሮ የቀጠለ ሲሆን በዚህ ተጋድሎም አገዛዙ ለሁለት ዓመት የሰሜን ወሎ ዞን የጦር ማዘዣ ጣቢያ አድርጎት የነበረው የግዳን ወረዳ ሙጃ ከተማ በርካታ ምሽጎችን በመስበር በምኒልክ ዕዝ ሰራዊት በቁጥጥር ስር ውሏል።
በዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው) በትላንትናው ዕለትና በዛሬው ዕለት ነጻ የወጡ ቦታዎች:-
• ሰሜን ወሎ ዞን ግዳን ወረዳ ዋና መቀመጫ የሆነችው ሙጃ ከተማ ጨምሮ ሙሉ ለሙሉ ወረዳው በፋኖ ቁጥጥር ስር ገብቷል።
• ⁠ሰሜን ወሎ ዞን ጋዞ ወረዳ መቀመጫ የሆነችው አስታይሽን ጨምሮ ወረዳው ሙሉ በሙሉ በፋኖ ቁጥጥር ስር ገብቷል።
• ⁠ሰሜን ወሎ ዞን ራስ አንጎት ወረዳ መቀመጫ የሆነችውን አሁን ተገኝ ከተማን ጨምሮ ሙሉ በሙሉ በፋኖ ቁጥጥር ስር ገብቷል።
• ⁠ሰሜን ወሎ ዞን ላስታ ወረዳ ብልባለ ከተማን ጨምሮ ከሹምሽሃ ቀበሌ ውጭ በፋኖ ቁጥጥር ስር ገብቷል።
• ⁠ሰሜን ወሎ ዞን ጉባላፍቶ ወረዳ ከወልደያ ከተማ ውጭ ያለው ሙሉ በሙሉ በፋኖ ቁጥጥር ስር ውሏል።
• ⁠ሰሜን ወሎ ዞን ዳውንት ወረዳ ዋና መቀመጫ የሆነችው ኩርባ ከተማን ጨምሮ ወረዳውን ሙሉ በሙሉ በፋኖ ቁጥጥር ስር ገብቷል።
• ⁠ሰሜን ወሎ ዞን ዋድላ ወረዳ ከኮን ከተማ ውጭ ያለው ሙሉለሙሉ በፋኖ ቁጥጥፍ ስር ገብቷል።
• ⁠ሰሜን ወሎ ዞን መቄት ወረዳ ከፍላቂትና ከገራገራ ከተማ ውጭ ያለው ሙሉ በሙሉ በፋኖ ቁጥጥር ስር ውሏል። ፍላቂትና ገረገራ ከተማ ላይ ትንቅንቅ እየተደረገ ነው።
ውጊያውና ትንቅንቁ አሁንም እንደቀጠለ ነው፣ ከመረጃው ብዛት የተነሳ ቁጥር ለመመዝገብ ተቸግረናል፣ ዝርዝር የቁጥር መረጃዎችን ይዘን የምንመለስ ይሆናል!
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው)
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
መስከረም 15/2018 ዓ.ም