የሙስሊም ወንድማማቾችንና “ሒዝብ ኡር ጣህሪር” የተባለውን ቡድን አሸባሪ ድርጅት በማለት ተፈረጁ

ኬንያ፣ የሙስሊም ወንድማማቾችንና “ሒዝብ ኡር ጣህሪር” የተባለውን ቡድን አሸባሪ ድርጅት በማለት ፈርጃለች።
ሙስሊም ወንድማማቾችን በአሸባሪነት ከፈረጁ አገራት መካከል፣ ግብጽ፣ ሳዑዲ ዓረቢያ፣ የተባበሩት ዓረብ ኢምሬቶች፣ ባሕሬን እና ሩሲያ ይገኙበታል። ሁለቱ ቡድኖች በአገሪቱ ውስጥ የሽብር ጥቃት መፈጸማቸውን የሚያሳይ መረጃ ባይኖርም፣ የአሸባሪነት ፍረጃው ግን ኬንያ የጽንፈኝነት ርዕዮተ ዓለምን ከወዲሁ ለመቅጨት የወሰደችው ርምጃ እንደኾነ ታምኖበታል። በፍረጃው መሰረት፣ የቡድኖቹ አባል መሆን፣ ለቡድኖቹ የገንዘብ መዋጮ ማሰባሰብ ወይም ከቡድኖቹ ጋር የተገናኘ ፕሮፓጋንዳ ማሠራጨት በወንጀል የሚያስጠይቁ ይኾናሉ።