ፌደራል መንግሥቱ በትግራይ ላይ ሌላ ዙር ጦርነት ለመክፈት ዝግጅት እያደረገ ይገኛል

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሌትናንት ጀኔራል ታደሠ ወረደ፣ ፌደራል መንግሥቱ በትግራይ ላይ ሌላ ዙር ጦርነት ለመክፈት ዝግጅት እያደረገ ይገኛል በማለት ዛሬ በኢትዮጵያ ከተመድ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ሃላፊ ጋር በተወያዩበት ወቅት መናገራቸውን የክልሉ ኮምንኬሽን አስታውቋል። ጀኔራል ታደሰ፣ ጊዜያዊ አስተዳደሩ የጦርነት ደመናን ለመግፈፍና ከፍተኛ ጥረት እያደረገ መሆኑን ለሃላፊው እንዳረጋገጡላቸው ቢሮው ገልጧል። በትግራይ በኩል የሚጀመር ጦርነት አይኖርም ያሉት ጀኔራል ታደሰ፣ ጊዜያዊ አስተዳደሩ በትግራይ የተሟላና ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ከፌደራል መንግሥቱ፣ ከዓለማቀፍ ድርጅቶችና ከውጭ ዲፕሎማቶች ጋር የቅርብ ግንኙነት በማድረግ ላይ መሆኑንም ገልጸዋል ተብሏል።