በደሴ ዙሪያ ከፍተኛ ውጊያ እና ድሉ

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምንሊክ ዕዝ ልጅ እያሱ ኮር ቤተ-አማራ ክፍለ ጦር በደሴ ዙሪያ ከፍተኛ ውጊያ በማድረግ ድል ተቀናጁ፡፡
በቀን 11/01/2018 ዓ.ም እና በቀን 12/01/2018 ዓ.ም በደሴ እና በግሸን ዙሪያ ጠላት በከባድ መሳሪያ የታገዘ ዉጊያ ቢከፍትም የቤተ-አማራዎቹ ንስሮች ከፍተኛ ድል እየተቀናጁ ይገኛሉ::
አገዛዙ አመታዊ ግሸን ደብረ ከርቤ ክብረ በዓል በፋኖ መከበር የለበትም በሚል እብሪት ከደሴ ከተማ ውስጥ ጀምሮ እስከ አምባሰልና ተለያየን ዙ23ን ጨምሮ የተለያዩ ከባድ መሳሪያዎችን እየተጠቀመ ቢሆንም በነበልባሎቹ ቤተ-አማራ ልጆች በአግባቡ እየተመከተ እና በመልሶ ማጥቃት በርካታ የጠላት ሃይል ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ብሎም ይዞታቸውን በማስከበር ድል እየተቀዳጁ ይገኛሉ::
ተጋድሎው ለሁለት ተከታታይ ቀናት ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን በዛሬው ዕለት ንጋት ጀምሮ ጠላት ከኩታበር እና ደላንታ ያመጣውን ሃይል ይዞ ውጊያ ቢያደርግም ተለያየን ላይ አይቀጡ ቅጣት ተቀጥቶ ለማፈግፈግ ተገዷል:: ጠላት በደረሰበት ሽንፈት ምክንያት እየሸሸ ባለበት ሁኔታ ንስሮቹ እንዳይከተሉት ቢራ የጫነ ተሳቢ መኪና ጎማ በመምታት መንገድ ዘግቶ ውሏል::
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ