“አድማ ብተና ግልገል ፋኖ ነው፡ ካሁኑ መጥፋት አለበት” የመከላከያ ሰራዊት አዛዦች!
የአገዛዙ ወታደሮች በተስፋ መቁረጥ ተሞልተዋል። በለስ የቀናቸው ከስምሪት ቀጠናቸው እየጠፉ ሕይወታቸውን ሲታደጉ፡ ይሄንን ወርቃማ እድል ማገኘት ያልቻሉት ደግሞ እርስ በእርሳቸው ተኩስ ከፍተው እየተገዳደሉ ነው።
መከላከያ ሰራዊቱ የቡድን መሣሪያ ጭምር አዙሮ በመተኮስ በርካታ የሚሊሻና አድማ ብተና አባላትን ገድሏል።
የግጭቱ መነሻ “በተሳሳተ መንገድ እየመራችሁ ወስዳችሁ በፋኖ እንድንጠቃ አድርጋችሁናል” በሚልና “በውጊያ ወቅት በቂ እገዛ እያደረጋችሁልን አይደለም” በሚሉ ምክኒያቶች ነው ተብሏል።
የመከላከያ ሰራዊት አዛዦችም “አድማ ብተና ግልገል ፋኖ ነው፡ ካሁኑ መጥፋት አለበት” የሚል መመሪያ መስጠታቸው ተሰምቷል።