ቅንጅት ተመሰረተ

ኢሕአፓ፣ መኢአድ፣ እናት ፓርቲ፣ አንድ ኢትዮጵያ ዲሞከራሲያዊ ፓርቲና የአማራ ግዮናዊ ንቅናቄ ቅንጅት መስርተዋል።

ፓርቲዎቹ ቀድም የመሠረቱት፣ ኃይላቸውን ለማሰባሰብና በምርጫ ወቅት ትብብር ለማድረግ መኾኑን የኢሕአፓ ዋና ጸሐፊ ሚስጥረሥላሴ ታምራት ለዋዜማ ተናግረዋል፡፡

ኾኖም ፓርቲዎቹ በቀጣዩ ምርጫ ስለመሳተፍ ገና ያልወሰኑ ሲኾን፣ ቅንጅቱ ወደፊት አስቻይ ኹኔታ መኖር አለመኖሩን አጥንቶ ይወስናል ተብሏል።

ቅንጅቱ መስከረም 10 በይፋዊ ፊርማ እውን እንደሚሆን ሰምተናል፡፡