አብዱራህማን መሃዲ የሚመሩት የኦብነግ አንጃ፣ ሰሞኑን ይፋ ከሆነው የ12ኛ ክፍል ፈተና ከ97 በመቶው በላይ የሶማሌ ክልል ተማሪዎች መውደቃቸው “አስደንጋጭ ክልላዊ ውድቀት” ነው በማለት ቅሬታውን ገልጧል። ፈተናውን ከወሰዱት 16 ሺሕ 779 ተማሪዎች ያለፉት 462ቱ ብቻ መሆናቸውን አንጃው ጠቅሷል። አንጃው፣ የተማሪዎች ዝቅተኛ ውጤት፣ ገዥው ፓርቲ በሶማሌ ክልል ላይ የሚያራምደው አድሏዊ አሠራር እና የክልሉ ባለስልጣናት የተዘፈቁበት ሙስና ውጤት ነው በማለትም ከሷል።