የሶማሌ ክልል የጸጥታ ኃይል አባላት በኦሮሚያ በፈጸሙት ጥቃት ሰዎች ተገደሉ

በኦሮሚያ ክልል በምሥራቅ ሐረርጌ ዞን ጭናቅሰን ወረዳና በምዕራብ ሐረርጌ ዞን ዶባ ወረዳ   የሶማሌ ክልል የጸጥታ ኃይል አባላት ናቸው የተባሉ አካላት በፈጸሙት ጥቃት የአምስት ሰዎች ሕይወት ማለፉን ተሰምቷል።

በጥቃቱ ሕይወታቸው ያለፈው የጭናቅሰን ወረዳ ነዋሪዎች መሆናቸውን ያስረዱት ምንጮች፣ በሌሎች ስድስት ሰዎች ላይ ደሞ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን ገልጸዋል።

ጳጉሜን 5 ላይም፣ በዶባ ወረዳ “ኩርፋ መቱ” ቀበሌ የታጠቁ ኃይሎች ባደረሱት ጥቃት ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ሰዎች አካላዊ ጉዳት ደርሶባቸዋል ተብሏል።