የሽግግር ፍትሕ ሒደት ባለበት መቆሙና የሰብዓዊ መብቶች አያያዝ እንዳሳሰባቸው 42 አገሮች ለተመድ አስታወቁ

አውስትራሊያን ጨምሮ የምዕራብና የምሥራቅ አውሮፓ አገሮች ያሉበት የ42 አገሮች ቡድን፣ በኢትዮጵያ የተጀመረው የሽግግር ፍትሕ ሒደት ባለበት መቆሙና የሰብዓዊ መብቶች አያያዝ ሁኔታ እንዳሳሰባቸው ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) አስታወቁ፡፡

በጀኔቭ ስዊዘርላንድ እ.ኤ.አ. ከመስከረም 8 ቀን 2025 እስከ ጥቅምት 8 ቀን 2025 ድረስ እየተካሄደ ባለው 60ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ምክር ቤት ጉባዔ፣ ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ አባል አገሮች እየተሳተፉበት ይገኛሉ፡፡

ከቀናት በፊት ኢትዮጵያን በተመለከተ የጋራ መግለጫ ካወጡ አገሮች መካከል ፈረንሣይ፣ ቼክ ሪፐብሊክ፣ ዩናይትድ ኪንግደም፣ ጀርመን፣ ስዊዘርላንድ፣ ኖርዌይ፣ ዩክሬን፣ አውስትራሊያ፣ አየርላንድ፣ ቡልጋሪያ፣ ሞልዶቫ፣ ስዊድንና አውስትራሊያን ጨምሮ 42 የአውሮፓ ኅብረት አባል አገሮች ይገኙበታል፡፡

በዚህ ጉባዔ ኢትዮጵያን በተመለከተ የሰብዓዊ መብት ሁኔታው አሳሳቢ መሆኑን አገሮቹን ወክሎ ሪፖርት ያቀረበው የአውሮፓ ኅብረት፣ በኢትዮጵያ ያለው የሰብዓዊ መብት ሁኔታ እንዳሳሰበው ገልጿል፡፡ ‹‹ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ፣ ሰላማዊ ሠልፍ የማድረግና የመደራጀት መብት ከመጪው ምርጫ አስቀድሞ መገደባቸው ያሳስበናል፤›› ብሏል፡፡ ኢትዮጵያ መጪውን አገራዊ ምርጫ በተያዘው ዓመት አሥር ወራት ውስጥ ታካሂዳለች ተብሎ ይጠበቃል፡፡ … ዝርዝሩ እዚህ ያገኙታል https://ethiopianreporter.com/145830/