ብሔራዊ ባንክ እያለሁ ከአይኤምኤፍ ጋር በነበረው ድርድር ከፍተኛ ተፎካካሪ ሆኜ ብዙ ነገሮችን በማስቀየር ውጤት አግኝቼበታለሁ

ብሔራዊ ባንክ ትልቁ ትምህርት ቤት ነው፣ ሁሉም ነገር እዚያ ነው ያለው፡፡ ዕድለኛ ነኝ ያልኩበት አንዱ ምክንያት ከአይኤምኤፍ ጋር በነበረው ድርድር ገና ጀማሪ ሆኜ ለአገሬ በጣም ከፍተኛ ተፎካካሪ ነበርኩ፡፡ ውጤትም አግኝቼበታለሁ፡፡ ብዙ ነገሮች አስቀይሬያለሁ፡፡ በድርድራችን ጊዜ አይኤምኤፍ አሸንፎን አያውቅም፡፡ …በልማት ባንክ  ሥራ ስጀምርም የባንኩን ሠራተኛ ወደ አንድ የሚያመጣ ሥራ ሠርቻለሁ፡፡ አንድም ሠራተኛ አላባረርኩም፡፡ ሠራተኛው ሥራውን በፍቅር እንዲገባበት ተደረገ፣ ውጤት እያየ ሲመጣ ደግሞ አገልግሎቶች ከላይ እስከ ታች የተናበቡ ሆኑ፡፡ የባንኩ ፖሊሲ እስከተፈጸመ ድረስ ፕሬዚዳንት ስለሆንኩኝ ገደብ የለሽ ሥልጣን አልወሰድኩም፡፡ ዋናው ቁጥጥሬ ፖሊሲው በአግባቡ እየተተገበረ መሆን አለመሆኑ ላይ ነው፡፡ ችግር ካለና ከሠራተኞች አቅም በላይ የሆነ ነገር ካለ እሱን መፍታት ነው፡፡ የሚሰርቅና የሚያጭበረብረውን ደግሞ ቦታ እንዳይኖው ነው ያደረግኩት፡፡ እንዲህ በመሥራት ነው ለውጡና ዕድገቱ የመጣው፡፡ …በየቦታው የተበለሻሸ ነገር ነበር፡፡ ሁለተኛው የመንግሥት ከመጠን ያለፈ ጣልቃ ገብነት ነበር፡፡ ከጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ ይደወልና ለእከሌ ብድር ስጠው ይባል ነበር፡፡ ሰንሰለቱ በጣም የተንዛዛ ነበር፡፡ የተናበበ ሲስተም አልነበረውም፡፡ የአሠራር ፖሊሲ አልነበረም፡፡ ብዙ ችግር ነበር፡፡ የመንግሥትን ዓላማ አቅጣጫ ይዤ ባንኩ የተሰጠውን ተልዕኮ ማስፈጸም ሥራዬ ነው፡፡ ስለአገር አቅም መከራከር ሥራዬ ነው፡፡ ከውጭም ይምጣ እዚህ አገር ያለም ዜጋ ይሁን፣ ትልቅም ሆነ ትንሽ ኢንቨስተርም ይሁን የአገር ጥቅም መቅደም ስላለበት በዚያ አግባብ ነበር የምሠራው፡፡ …ዝርዝር ዘገባውን በዚህ ሊነክ ይመልከቱ፡፡