ኬንያ የ42 የቴሌቪዥን ጣቢያዎችን ፈቃድ ልትሰርዝ ነው።

ኬንያ የ42 የቴሌቪዥን ጣቢያዎችን ፈቃድ ልትሰርዝ ነው።

የኬንያ የኮሚዩኒኬሽን ባለስልጣን በ7 ቀናት ውስጥ የ42 የቴሌቪዥን ጣቢያዎችን ፈቃድ ሊሰርዝ መሆኑ ተነግሯል።

ባለስልጣኑ ፈቃዳቸው ሊሰረዝ የሚችልን ጣቢያዎች ዝርዝር ይፋ ሲያደርግ ፈቃዳቸው ከተሰረዘ በኋላ ምንም ስራ ማከናወን እንደማይችሉ ገልጿል።

የኮሚዩኒኬሽን ባለስልጣኑ የኬንያን የመረጃ ህግ የሚጥሱ ተቋማት በጋዜጣ ከተነገረ በኋላ በ7 ቀናት ውስጥ ፈቃዳቸው ሊሰረዝ እንደሚችል ሲያነሳ በዋነኝነት ያልተገባ ይዘት ማሰራጨት፣ የማሰራጫ መሰረተ ልማት አለመኖርና የፈቃድ ክፍያ አለመክፈል ፈቃድ ሊያሰርዙ ይችላሉ።

ከወራት በፊት የቤቲንግ ቁጥጥር እና ፈቃድ ቦርድ 23 የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ከስፖርታዊ ውርርድ ጋር በተያያዘ የወጣውን የማስታወቂያ መመሪያ በመጣሳቸው ሊዘጉ እንደነበር አስጠንቅቆ ነበር።

ጣቢያዎቹ የስፖርት ውርርድ ማስታወቂያ እንዳይተወወቅ ቢታገድም ማስታወቂያዎችን ማሳየት መቀጠላቸውን ቦርዱ ገልፆ ነበር።

42 የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ፈቃድ መሰረዝ በባለፈው የፈረንጆቹ መስከረም 12 በጋዜጣ የወጣ ሲሆን በመጪዎቹ 7 ቀናት ውስጥ ይፈፀማል ተብሎ ይጠበቃል።

ጎረቤት ሃገር ኬንያ በ2023 በአጠቃላይ 135 (https://youtu.be/vyCHx1WJfMg?si=zyPPwWoC-zawEPd-) የቴሌቪዥን ጣቢያዎችና 225 የሬዲዮ ጣቢያዎች የነበሯት ሲሆን በዋነኝነት መቀመጫቸውን በዋና ከተማዋ ናይሮቢ ያደረጉ ናቸው።

ዘገባው የKenyans ነው።