የፋኖ አመራሮችን ለማስገደል ተልዕኮ ተሰጥቶት የነበረው የደህንነት አባል እጅ ከፈንጅ ተያዘ!
የደህንነት አባሉ የፋኖ አመራሮች ያሉበትን ቦታ ጥቆማ በመስጠት በድሮን ለማስገደል እንዲሁም የፋኖ ሎጅስቲክ ማከማቻ ናቸው ብሎ የሚያስባቸው ቦታዎችን ለድሮን ተኳሾች ጥቆማ በመስጠት የማውደም ተልዕኮ ተሰጥቶት ነበር ተብሏል።
የደህንነት አባሉ፡ በአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና አርበኛ በላይ ዘለቀ ዕዝ 4ኛ ደጃች ኮር ስር የሚገኘው ዋዋ ጎቤ ክ/ጦር በሚንቀሳቀስበት ቀጠና ሲቪል ልብስ በመልበስ በአካባቢው ሲንቀሳቀስ ነው በቁጥጥር ስር የዋለው ሲሉ የክፍለ ጦሩ አመራሮች አስታውቀዋል።
የደህንነት አባሉ መሐመድ ዋዮ ዎቴ በሚል ስም የሚጠቀም መሆኑንና የመከላከያ ሰራዊት አባል እንደሆነ በኪሱ ከያዘው መታወቂያ ለማረጋገጥ ተችሏል።