በአርማጭሆ ቀጠና ልዩ ስሙ ኩርቢ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ከባድ ተጋድሎ ሲደረግ መዋሉ ታውቋል።

በአርማጭሆ ቀጠና ልዩ ስሙ ኩርቢ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ከባድ ተጋድሎ ሲደረግ መዋሉ ታውቋል።
የአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ ደጃዝማች ኮር በሻለቃ እሸቴ አሸብር የሚመራው ደጀን አሸብር ክፍለጦር በአርማጭሆ ቀጠና ልዩ ስሙ ኩርቢ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ላይ ዛሬ ጳጉሜ 03/2017 ዓ/ም ከንጋት ጀምሮ ከባድ ትንቅንቅ ሲያደርግ መዋሉን መረብ ሚዲያ ማረጋገጥ ችሏል።
በዚህ ውጊያ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ የጠላት ብልፅግና ቡድን ወታደሮች የተገደሉ ሲሆን፡ እገዛ ለማድረግ ከወደ ሳንጃ ከተማ ተነስቶ ወደ ክርቢ ለመግባት ሲገሰግስ የነበረው ኃይልም የደፈጣ ጥቃት ተፈፅሞበት ከፍተኛ የሆነ የሰብአዊና ቁሳዊ ውድመት አስተናግዶ ወደ መጣበት መፈርጠጡ ታውቋል።
ስለውጊያው ዝርዝር ውጤት የዕዙ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ መረጃ ሲያወጣ ጠብቀን ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።