ታሪካዊው ዲማማ ዲክላሬሽን በተፈፀመባት ታሪካዊቷ ዲማማ ቀበሌ ላይ በርካታ የአገዛዙ ወታደሮች መገደላቸው ተሰማ!
በምዕራብ አማራ ቀጠና ፋግታ ለኮማ ወረዳ ስር በምትገኘው ድማማ ቀበሌ ማዘዣ ጣቢያቸውን አድርገው በነበሩ የአገዛዙ ወታደርች ላይ ዛሬ ጳጉሜ 03/2017 ከንጋት ጀምሮ በተወሰደ እርምጃ በርካታ ወታደሮች ሲገደሉ በርካቶች መቁሰላቸውን መረብ ሚዲያ ከዕዙ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ለማረጋገጥ ችሏል።
በአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና አፄ ቴዎድሮስ ዕዝ ጎጃም አገው ምድር ክ/ጦር ስር የሚገኙት የአሥር አለቃ ኤፍሬም አጥናፉ ብርጌድ እና ራስ ቢትወደድ መንገሻ ጀምበሬ ብርጌድ አባላት ዛሬ ከንጋት ጀምሮ በወሰዱት እርምጃ ዘጠኝ ወታደሮች ሲገደሉ ከ12 በላይ የሚሆኑት ደግሞ መቁሰላቸው ተረጋግጧል።
በጥቃቱ በተለይ በዲማማ ቀበሌ ልዩ ስሙ ማንጉዳት ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ላይ የነበረው የጠላት ማዘዣ ካምፕ የወደመ ሲሆን በርካታ የጦር መሣሪያዎችም በፋኖ እጅ መግባታቸው ታውቋል።
የፋግታ ለኮማ ወረዳዋ ዲማማ ቀበሌ የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ኃይል እና የአማራ ፋኖ ጎጃም ዕዝ ውህደት የፈፀሙባት፣ የጎጃም ፋኖ አንድነት ማሰሪያ ገመድ የተቋጠረበት ዲማማ ዲክላሬሽን የተፈፀመባት ታሪካዊት ቦታ ናት።
የጎጃም ፋኖ አንድነት ፅንስ ተፀንሶ በተወለደባት በዚች ታሪካዊት ስፍራ ሰፍረው በነበሩ የፀረ አማራው አገዛዝ ተላላኪ ወታደሮች ላይ እርምጃው የተወሰደው።
ዲማማ ለሚገኘው ኃይል እገዛ ለማድረግ መነሻቸውን ከእንጅባራ፣ ከአዲስ ቅዳም፣ ከጎመጅ ተራራ እና ከጊሳ ከተማ ያደረጉ ዙ23ና ሌሎች ከባባድ የጦር መሣሪያዎችን የታጠቁ የአገዛዙ ኃይሎች ካሰቡበት ሳይደርሱ ከወደ ፋኖ በተሰነዘረባቸው ጥቃት ብትንትናቸው ወጥቶ እርስ በእርሳቸው ሲታኮሱ መዋላቸው ታውቋል።