የባህል ስብጥር ባለበት አገር culture apartheid ያዛልቃል? ( ያሬድ ኃይለማርያም)

የባህል ስብጥር ባለበት አገር culture apartheid ያዛልቃል? ( ያሬድ ኃይለማርያም)
+++
የአገዛዝ ሥርዓቱ አይን ባወጣ መንገድ እየፈጸመ ያለው Cultural Apartheid ከወዲሁ እልባት ሊበጅለት ካልቻለ በማህበረሰቦች መካከል ቁርሾን፣ መቃቃርና ጤናማ ያልሆነ ግንኙነት እንዲስፋፋ ያደርጋል። እንደ ኢትዮጵያ ባለ እጅግ የተሰባጠረ ባህልና የማንነት መገለጫዎች ያሉትን ሕዝብ የሚያስተዳድር መንግስት ሁሉንም በዓላት በእኩልነትና በአገር የባህል ቅርስነት ቆጥሮ እኩል ማስተናገድ ሲገባ የተወሰኑ ማህበረሰቦችንና በአላትን በውክቢያ፣ በክልከላ፣ በእስርና እንግልት ዜጎች ባህላቸውን በነጻነትና በደስታ ያለ ፍርሃት እንዳያከብሩ እየከለከለ ሹመኞች የእኔ የሚሉትን በዓል ደሞ ከፍተኛ የመንግስት በጀት መድቦና ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ መንግስታዊ ክብረ በዓል ማስመሰል የአፍሪካ መዲና በምትባል ከተማ ውስጥ Cultural Apartheid ማካሄድ ነው።
የአሸንዳ፣ አሸንድዬና ሻዳይ በዓልን ከአመታት በፊት በዪኔስኮ ጭምር እንዲመዘገብ እሰራለሁ ያለ መንግስት በአሉ በአደባባይም ሆነ በአዳራሾች እንዳይካሄድ ከልክሏል። ያም አልበቃ ብሎ በራሳቸው ገንዘብ ባዕሉን ማክበር የሚፈልጉ ወጣቶች በአዲስ አበባ በተለያዩ ሆቴሎች ተሰባስበው ሊያከብሩ ያደረጉት ጥረት ለዚሁ በተመደቡ ፖሊሶችና የደህንነት ሃይሎች እየተዋከቡና እየተገፈተሩ ተባረዋል። በወቅቱ የታሰሩም አስተባባሪዎች ነበሩ። ይህ አስነዋሪ ድርጊት በተፈጸመ በሳምንቱ ደግሞ በአዲስ አበባ በፊት ተከብሮ የማያውቅና ለሁለተኛ ጊዜ የተከበረውን ተመሳሳይ የኦሮሞ ወጣት ሴትች በአል መንግስት እጅግ ከፍተኛ በጀት መድቦ፣ ለወጣቶቹ አንድ አይነት ልብስ አልብሶ፣ ከየመጡበት የሚያመላልሱ አውቶቢሶችን መድቦ፣ አበል ከፍሎ፣ ደግሶ፣ አውራ ጎዳናዎችን ዘግቶና ከፍተኛ የጸጥታ ጥበቃ መድቦ በአሉን መንግስታዊ ቬስቲቫል በሚመስል መልኩ አክብሯል።
የኦሮሞ ወጣት ሴቶች በአል በዚህ ደረጃ መተዋወቁና መከበሩ እሰየው የሚያስብልና መከበርም እንዳለበት አስረግጠን ሴኩላር መሆን የተሳነውና እና ለሁሉም የሕዝብ በዓላትና የመገለጫ እሴቶች እኩል ክብርና ትኩረት ለመስጠት የዘረኝነት እሳቤው ያገደው የብልጽግናው አመራር አለም በሚታዘበው ደረጃ የአፍሪካ መዲና በሆነችው በአዲስ አበባ Cultural Apartheid ወይም የባህል አፖርታይድን እያካሄደ መሆኑን እና ወደፊት የሚያመጣውን መዘዝ የተረዳው አልመሰለኝም።
UNESCO Stop cultural apartheid in Ethiopia!