በሕዳሴ ግድብ በተፈጠረው ውዝግብ ዙሪያ ሌሎች የተፋሰሱ አገራት አያገባቸውም! ( ግብጽና ሱዳን )

የግብጽና ሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች፣ በኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በተፈጠረው ውዝግብ ዙሪያ ሌሎች የተፋሰሱ አገራት አያገባቸውም ሲሉ ካይሮ ውስጥ ትናንት ባወጡት የጋራ መግለጫ አስታውቀዋል።

ኹለቱ አገራት ግድቡ በምሥራቅ የናይል ተፋሰስ አገራት ላይ ዘላቂ ስጋት ደቅኗል በማለት ስጋታቸውን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ ለግድቡ የውሃ ሙሌት ወስደዋለች ያሉትን የተናጥል ርምጃ የተቃወሙት ኹለቱ አገራት፣ የውሃ ደኅንነታቸው “አንድ” እና “የማይነጣጠል” መኾኑን አጽንዖት ሠጥተዋል።

ኢትዮጵያ በምሥራቃዊ የናይል ተፋሰስ ዙሪያ የምትከተለውን ፖሊሲ መቀየር እንዳለባትም ኹለቱ አገራት አሳስበዋል።