የሕወሓት ታጣቂዎች በደቡባዊ ትግራይ ዞን በሰላማዊ ሰዎች ላይ ተኩስ ከፈቱ

የሕወሓት ታጣቂዎች በደቡባዊ ትግራይ ዞን መኾኒ ከተማ ትናንት በሰላማዊ ሰዎች ላይ ተኩስ አንድ ወጣት ሲገድሉ ኹለቱን ማቁሰላቸውን የአካባቢው ምንጮች ለዋዜማ ተናግረዋል። ሟቹ በጥይት ተመቶ ከወደቀ በኋላ በተደጋጋሚ በታጣቂዎቹ ጥይት መመታቱን ምንጮች ገልጸዋል።

የጸጥታ ኃይሎቹ ተኩስ የከፈቱት፣ የአካባቢው ማኅብረሰብ እያቀረበባቸው ያለውን ተቃውሞ ለማፈን ነው ብለው እንደሚያምኑም ምንጮች ተናግረዋል።

በተያያዘ፣ በአላማጣ ከተማ አንድ የቀበሌ አስተዳዳሪ በታጣቂዎች ተደብድቦ ወደ ካምፕ እንደተወሰደ በአማራ ክልል በኩል ለከተማዋ ከንቲባነት ተሹመው የነበሩት ሃይሉ አበራ ነግረውናል።