መመሪያው የክፍያ ጭማሪ፣ የአደጋ ዋስትና ክፍያና የመኖሪያ ቤት ኪራይ ድጎማ ጥያቄዎችን አልመለሰም ( የጤና ባለሙያዎች )

ጤና ሚንስቴር፣ ከመስከረም ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ አዲስ የጤና ባለሙያዎች የጥቅማ ጥቅም መምሪያ አውጥቷል። መመሪያው፣ በክልሎችና ፌደራል ደረጃ የጤና ባለሙያዎች የጤና መድኅን ሽፋን መጠቀሚያ ቁጥር እስኪያገኙ ድረስ ከእነ ቤተሰባቸው ነጻ የሕክምና አገልግሎት እንዲያገኙና ለዚህም አገልግሎት የሠራተኛ ክሊኒኮች እንዲለዩ ያዛል። መመሪያው፣ የጤና ባለሙያዎች የትርፍ ሰዓት ክፍያ በመንግሥት ሠራተኞች አዋጅና በሲቪል ሰርቪስ የትርፍ ሰዓት ሥራ የክፍያ ተመንና የማካካሻ እረፍት መመሪያ መሠረት እንዲፈጸምም ይጠይቃል። የጤና ባለሙያዎች ጥያቄ አስተባባሪ ቡድን ግን፣ መመሪያው የክፍያ ጭማሪ፣ የአደጋ ዋስትና ክፍያና የመኖሪያ ቤት ኪራይ ድጎማ ጥያቄዎችን አልመለሰም በማለት ተችቷል።