ዘመድ የታፈነባችሁ ኮልፌ ፖሊስ ማሰልጠኛ አፈላልጉ። በመቶውች እዛ በድብቅ ታግተው ይገኛሉ። ( ጃዋር መሐመድ )

ሰሞኑን ለየት ያለ አግዶ የመዘርፊያ ስልት መጥቷል። ከዚህ በፊት ሰው ታግቶ ወደ ዱር ተወስዶ ገንዘብ ይጠየቅ ነበር። አሁን ግን የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ከመዲናዋ ሰውን አፍነው እዚያው ከተማዋ ውስጥ ይደብቃሉ። ወደ ፍርድ ቤት አይወስዱትም ፤ ለቤተሰቦቹም አያሳዩም።

ቤተሰብ በፍለጋ ሲጨነቅ ፣ የደህንነቶቹ ደላላዎች በመደወል ገንዘብ ከተሰጣቸው ያሉበትን ቦታ እንደሚነግሩ በስልክ ለቤተሰብ ያሳውቃሉ። ያ ገንዘቡ ከተከፈለ በኋላ ደግሞ ከቤተሰቡ ጋር ለማገናኘት ተጨማሪ ገንዘብ ይጠየቃል። ከዚያ በኋላም ለመልቀቅም በእጥፍ ገንዘብ ያስከፍላላኡ። ወዳጅ ዘመድ ሚስጥር ቢያወጣ ታፋኙ እንደሚገደል ያስፈራራሉ። ህዝባችን መንግስታዊ ካባ በለበሱ ሌባ ዱርዬዎች መጫወቻ ሆነ።

ለማንኛውም ዘመድ የታፈነባችሁ እስኪ ኮልፌ ፖሊስ ማሰልጠኛ አፈላልጉ። በመቶውች እዛ በድብቅ ታግተው ይገኛሉ። ( ጃዋር መሐመድ እንደፃፈው)