የኬንያው ባንክ፣ ከኢትዮጵያ የግል ባንክ የአክሲዮን ድርሻ ለመግዛት ንግግር ጀመረ

የኬንያው “ኬሲቢ” ባንክ፣ ከአንድ ስሙ ይፋ ካልሆነ የኢትዮጵያ የግል ባንክ የአክሲዮን ድርሻ ለመግዛት ንግግር መጀመሩን ዳይሊ ቢዝነስ ዘግቧል። ኬሲቢ፣ በ18 ወራት ውስጥ ከባንኩ ለመግዛት የወሰነው 40 በመቶ የአክሲዮን ድርሻ መሆኑን ዘገባው ጠቅሷል።

ኬሲቢ አክሲዮን መግዛትን የመረጠው፣ በአገሪቱ የፋይናንስ አገልግሎት ተጠቃሚው ሕዝብ 46 ነጥብ 5 በመቶ ብቻ በመሆኑና በዲጂታል ዘዴዎች አማካኝነት በቁጠባ ረገድ የሚገጥመውን ፉክክር ለማስቀረት ነው ተብሏል።