11 ክልል ዓቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጥምረት መስርተዋል።

11 ክልል ዓቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ ጉዳዮች ዙሪያ ለመተባበር ያስችለናል ያሉትን ጥምረት መስርተዋል።

በጥምረቱ ምስረታ ሂደት ከ20 በላይ ፓርቲዎች ቢሳተፉም፣ እስከፍጻሜው የዘለቁት ግን 11ዱ ብቻ ናቸው።

የጥምረቱ መስራቾች አናሳ ብሔረሰቦችን የሚወክሉ ሲሆኑ፣ ከእነዚህም መካከል የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ፣ የአፋር ነጻ አውጭ ግንባር፣ የጋሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ፣ የአገው ብሔራዊ ሸንጎ፣ የካፋ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅትና የጋምቤላ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ይገኙበታል።