የውጪ ዜጎች ለሕክምና እጥፉን እንዲከፍሉ ሊደረግ ነው ተባለ

ጤና ሚንስቴር፣ የውጭ ዜጎች በመንግሥት የጤና ተቋማት ለእያንዳንዱ አገልግሎት የወጣውን ተመን እጥፍ እንዲከፍሉ የሚያስገድድ መመሪያ ማውጣቱን ሪፖርተር ዘግቧል። መመሪያው፣ የዩኒቨርስቲ ሆስፒታሎች የአገልግሎት ተመኑን በየሦስት ዓመቱ እንዲከልሱ እንደሚያዝ ዘገባው ጠቅሷል።

 

በክልሎች የሚገኙ ሆስፒታሎች የሚያደርጉት ክለሳ ደሞ የሕዝቡን የመክፈል አቅም ታሳቢ እንዲያደርግ፣ የጤና ተቋማትን ደረጃና የሚገኙበትን ቦታ ከግምት እንዲያስገባ ያዛል ተብሏል።

 

የመድኃኒትና ሌሎች አላቂ የሕክምና ቁሳቁሶች ዋጋ ትመናም፣ መጓጓዣን ጨምሮ ከ25 እስከ 30 በመቶ ተጨማሪ እንደሚደረግበት ደንቡ ላይ እንደሠፈረ ዘገባው አመልክቷል።