በኦሮሚያ ሹፌሩ ሲገደል 40 መንገደኞች ታገቱ

በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደገም ወረዳ ልዩ ስሙ “ኤግዱ” በተባላ ስፍራ ከአማራ ክልል ግንደወይን ከተማ ወደ አዲስ አበባ ሲያቀና ከነበረ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ላይ ታጣቂዎች ዛሬ ከ40 በላይ መንገደኞችን ማገታቸውንና ሹፌሩን መግደላቸውን ተሰምቷል።

ሹፌሩ ከእገታው ለማምለጥ ሲሞክር፣ አውቶብሱ ተገልብጦ በተወሰኑ ተሳፋሪዎች ላይ አካላዊ ጉዳት እንደደረሰ የዓይን እማኞች ተናግረዋል።