የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ሀይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ለተከታታ ሶስት ቀናት ከአብይ አህመድ ዙፋን ጠባቂ 101ኛ፣ 102ኛ፣ 103ኛ፣ 104ኛ ክ/ጦር አየር ወለድ ኮማንዶ፣ አድማ ብተና እና የሚኒሻ አባላት ላይ ከባድ ጉዳት አድርሷል።
በዚህ ከነሀሴ 8/2017 ዓ ም ጀምሮ እየተካሄደ ባለው አውደ ውጊያ የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ሀይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የአጼ ይኩኖ አምላክ፣ ሰባት ለሰባ እና ነጎድጓድ ክ/ጦር የተውጣጡ ሺ አለቃዎች በወሰዱት መብረቃዊ ጥቃት የጥላት ኃይል ሙትና ቁስለኛ ሁኗል።
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ሀይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው እዝ ከነሀሴ 8 -9/2017 ዓ ም ከሌሊቱ 11:00 ጀምሮ በድንጋይ ወድማ ግንባር ስብር ሽ አለቃ ከሰባት ለሰባ፣ 4ኛ ሽ አለቃ ከአጼ ይኩኖ አምላክ ክ/ጦር፣ በጉሎ ግንባር ከሰባት ለሰባ ደመላሽ ሽ አለቃ፣ ከነጎድጓድ ክ/ጦር መብረቁ ብርገድ ጠላት ካምፕ ድረስ ዘልቀው ሲገቡ በከርካሜ ተረተር ግንባር ደግሞ የአጼ ይኩኖ አምላክ 5ኛ ሺ አለቃ ባካሄዱት ኦፕሬሽን የጥላት ሀይል ጭዳ ተደርጓል።
በእብሪት አማራን ለመጨፍጨፍ በሸዋ ክ/ሀገር መንዝ ግንባር የገባው የብረሃኑ ጁላ ቀይ ምንጣፍ ሰራዊት ከነሀሴ 8-10/2017 ዓ ም በተወሰደበት የተቀናጀ ጥቃት 2 ፓትሮል አስከሬ እና አንድ አይሱዚ ቁስለኛ ሲታቀፍ በጉሎ አካባቢ ደግሞ አንድ ፓትሮል ቁስለኛ፣ አንድ አይሱዚ ሙሉ አስከሬ ሲጭን ከ40 በላይ ቁስለኞች መሀል ሜዳ ሆስፒታል አስገብቷል።
በተጨማሪም በካራ ቆሬ ጤና ጣቢያና ትምህርት ቤት በሰፈረው የአብይ አህመድ ምስለኔ ሰራዊት ላይ የአጼ ይኩኖ አምላክ ክ/ጦር አስራት ወ/ጌስ ብርገድ አምስተኛ ( አይሻ ሰይድ) ሺ አለቃ ሁለተኛ ሻምበል እና አሳልፍ ተሻገር ሺ አለቃ ሻምበል አንድ ነሀሴ 10/2017 ዓ ም ከምሽቱ 3:00 ጀምረው በወሰዱት የተቀናጀ ኦፕሬሽን የጥላት ሀይል ምሽጉን ለቆ መስጅድ እና ቤተክርስቲያን ሲገባ ሰባት ለሰባ ክ/ጦር ስበር ሺ አለቃ በላይኛው አጣየ በፈረድ ውሃ ቀበሌ መሽጎ በነበረው የጥላት ሀይል ላይ በወሰደው እርምጃ ጠላት አካባቢውን ለቆ ወደ ጨፋና ከሚሴ ፈርጥጧል።
ሰባት ለሰባ ከ/ጦር ስበር ሺ አለቃ ( ቃኚ) በ101ኛ ኮምንዶ ላይ በወሰደው ጥቃት የአብይ አህመድ ጀበና ሰባሪ ወደ ጨፋ ሸሽቶ ሲሄን አንድ የኮምንዶ አባል ስናይፕር ይዞ ፋኖን ተቀላቅሏል።
አውደ ውጊያው ዛሬም ለአራተኛ ቀን ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን የኦሮሞ ልዩ ዞን ሚኒሻ የአብይን ግትልትል ሰራዊት በማገዝ ተሳታፊ የሆነ ሲሆን ይህ መረጃ እስከተጠናከረበት ድረስ ጦርነቱ እንደቀጠለ ነው።
“ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን”
አፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የህዝብ ግንኙነት ክፍል
ነሐሴ 11/2017 ዓ.ም