“አቡነ ፋኑኤል የጎረጎሩት ዓሣ ዘንዶ ሆኖ ወጣ!” በሚል ርዕስ ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ ያቀርቡልን ጽሁፍ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንና በአጠቃላይ በአገሪቱ ላይ የተከፈተው የማፍረስና የማጥፋት ዘመቻ እጅግ እየተጧጧፈ በሚካሄድበት ወቅት ላይ ነው። በዚህም መሠረት የጥፋት ወጭቱ ውስጥ እጃቸውን ከከተቱት መካካል በዋናነት ዘንዘሪጡ ዳንኤል ክብረት፣ አባ ሰረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል፣ አቡነ ማትያስና አቡነ ፋኑኤል ይገኙበታል።
ከዚህ በታች የሰፈረችውን ጦማር የወቅቱን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማንያን፣ ገዳማት፣ የቆሎ ት/ቤቶች፣ካህናትና አገራችን ኢትዮጵያ ላይ እየተደረገ ያለውን የጥፋት ዘመቻ ፍንትው አድርጎ ያሳያል። ባለፈው ሳምንት በዘረኝነትና ፖለቲካ ያበዱት አቡነ ማቲያስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ሆነው በታላቁ ወንበር ላይ የተቀመጡ ቢሆንም “ድመት መንኩሳ ዐመሏን አትረሳ” ነውና ቤተ ክርስቲያኒቷን አውግዞ ላፈነገጠ በዘረኞችና ፖለቲከኞች የተፈጠረውን “መንበረ ሰላማ” መርቀው ከፍተዋል። ከዚህ መረዳት የሚቻለው አብይ አህመድና አቡነ ማቲያስ ሁለት አዲስ አገሮችን ማለትም ትግራይና ኦሮሚያን በማዋለድ ሂደት ውስጥ መሆናቸውንና ለዚህ እንቅፋት ይፈጥርብናል ያሉትን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን እየገነጣጠሉ መሆናቸውን ነው። በቅርቡም ብርሃኑ ጁላ ህወሃቶችን “በሰላም መገንጠል ትችላላችሁ እናሰናብታችኋለን” ብሎ የተናገረውን ማስታወስ ያስፈልጋል። ጽሁፉን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ። አቡነ ፋኑኤል የጎረጎሩት ዓሣ ዘንዶ ሆኖ ወጣ!