የፋኖ ታጣቂዎች ከነሐሴ 1 ጀምሮ በተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ላይ ክልከላ በተግባር ላይ ይገኛል።

በአማራ ክልል በምዕራብ፣ ምሥራቅና ሰሜን ጎጃም ዞኖች የፋኖ ታጣቂዎች ከነሐሴ 1 ጀምሮ በተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ላይ ክልከላ ጥለዋል በመባሉ፣ የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ መስተጓጎሉ ታውቋል።

በዚሁ ሳቢያ፣ ከክልሉ ወደ አዲስ አበባና በክልሉ ከተሞች መካከል የአሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ከትናንት ጀምሮ ምሽት ጀምሮ ተቋርጧል። ታጣቂዎቹ ክልከላ የጣሉት፣ የአብይ አገዛዝ  ከሐምሌ 5 ጀምሮ በምሥራቅ ጎጃም ዞን ከሞጣ ከተማ ወደ ባሕርዳር የሚወስደው ዋናው መንገድ ለጊዜው እንዲዘጋ ማዘዙን በመቃወም ነው ተብሏል።

ከሦስቱ ዞኖች ወደ አዲስ አበባ በማቅናት ላይ የነበሩ ከባድ የጭነት ተሽከርካሪዎችም በኦሮሚያና አማራ ክልል አዋሳኝ ፍልቅልቅ በተባለ ስፍራ ላይ፤ ከመሃል አገር የተነሱት ደሞ ክበገርበ ጉራቻ፣ ቱሉ ሚልኪ እና ጎሐጽዮን ከተሞች ላይ ቆመዋል።