አልሸባብ ከሞቃዲሾ 40 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ያለችን ከተማ ዳግም መያዙን ገለፀ።
አልሸባብ ባለፉት ቀናት ከሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ 40 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ባለችው ሳቢድ ከተማ ከባድ ውጊያ ማድረጉን ገልፆ በኡጋንዳ እና ሶማሊያ ጦር ላይ ከፍተኛ ጥቃት ሰንዝሮ ከተማዋን ዳግም መቆጣጠሩን ገልጿል።
በተጨማሪ አልሸባብ በከተማዋ ያለን የሶማሊያ ጦር እና የኡጋንዳ ሰላም አስከባሪ ጦር ማዘዣዎችን እንደዚሁም መኪኖችን እና መሳሪያዎችን መያዙን ገልጿል።
የሳቢድ ከተማን ከወር በፊት የሶማሊያና የኡጋንዳ ጦር ከአልሸባብ ነፃ አውጥተውት የነበረ ሲሆን ከተማዋ በአልሸባብ እጅ ዳግም በመወደቋ ላይ የሶማሊያ ጦርም ሆኑ የአፍሪካ ህብረት ተልዕኮ ያሉት ነገር የለም።
አልሸባብ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ኃይሉን እያጠናከረ በርካታ ከተሞችን መያዝ ሲጀምር በሶማሊያ ያለው የህብረቱ ተልዕኮ ከበጀት ድጋፍ ጋር በተገናኘ የሚፈልገውን ያህል እየተንቀሳቀሰ እንዳልሆነ ሲዘገብ መቆየቱ ይታወሳል።
Source: Somali Guardian